Intro
Amharisk • አማርኛ

ሉቨሊን ሪሀል ብረና

የመካከለኛ እና ሁተኛ ደረጃ ት/ቤት አገራዊ የወላጆች ኮሚቴ ኃላፊ (FUG)

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ስለ ኖርዌይ እና የልጆች አስተዳደግ ያለን አስተያየት በተመለከተ ማወቅ ያለባቸው ነገር ምንድን ነው?

ሁሉም ወላጆች ለልጆቻቸው የተሻለ ነገር ይፈልጋሉ ልጆቻቸው ደግሞ እራሳቸው ከነበራቸው ሕይወት የበለጠ የተሻለ ኑሮ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ።

ሕብረተሰቡ ከእነሱ የሚፈልገው ምን እንደሆነ ስደተኞች ማወቅ አለባቸው በዚህም የተቻለ መጠን በተገቢው መልኩ ልጆቻቸውን መከታተል ይችላሉ።

ት/ቤቶች ምን ይጠብቃሉ? ለሚለው እና የመዋእለ ሕፃናት ት/ቤቶች እና የሕዝባዊ ጤና ክሊኒኮች ምን ይጠብቃሉ? ለሚሉት ጥያቄዎች ለሕፃናቱ ጥቅም እና ለወላጅነት ኃላፊነታቸው በማለት በጥያቄዎቹ ማሰባቸው አስፈላጊ ነው።

«እኛ» እና «እኔ» በሚሉ ባሕሎች መካከል መቀያየር እንዲኖር ያለው የልጆች ችሎታ ምን ይመስላል?

በአመለካከቶች መካከል ያሉ ግጭቶች በብዙ ልጆች ግንኙነት መካከል ወሳኝ ነው። ቤት ውስጥ በጥሩ ነገር የሚያታይ ልጅ ምናልባት ት/ቤት ውስጥ ጥሩ ሆኖ ሊታይ አይችልም፣ እንዲሁም በተገላቢጦሽ። ወላጆች ብዙውን ጊዜ በልጆቻቸው ዙሪያ ተጨናቂ በመሆን በበለጠ በሐይማኖታዊ እና ባሕላዊ ልዩነቶች በአብዛኛው የተያዘ ነው። አሁን ያሉባቸው ሁኔታዎች ልጆች እራሳቸው የመረጧቸው እንዳልሆኑ ሊታወቅ ይገባል።

ማንኛውም አይነት አለመግባባት አጋጥሞሽ ያውቃልን?

ምሳሌ ልሰጣችሁ እችላለሁ። ልጅ በነበርኩበት ጊዜ ቤት ውስጥ ስሕተት በምፈጽምበት ወቅት አባቴ ስናገርሽ ወደታች ተመልከቺ አክብሪኝ በማለት ይናገረኝ ነበር። ት/ቤት ሥሕተት በምፈጽምበት ጊዜ ደግሞ መምህሬ ስናገርሽ ወደ አይኔ ተመልከቺ ይለኝ ነበር፡፡

ለወደፊቱ እንዲሆኑ የምትጠብቂያቸው ተስፋዎችሽ ምንድን ናቸው?

ስለ ልጆች በማለት በሰዎች እና እኩል ዋጋቸው መካከል ያለውን ተመሳሳይነት ማየት እንድንችል እፈልጋለሁ። ያሉ ልዩነቶችን ከመመልከት በላይ የበለጠ የሚያሳስብ ጉዳይ ነው።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no