Intro
Amharisk • አማርኛ

ጉልካን ኦዛልኝ

ድራመን ውስጥ የሚገኝ ት/ቤት መምሕር

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች የኖርዌይ ትምህርት በተመለከተ ማወቅ ያለባቸው አስፈላጊ ነገር ምንድን ነው?

ከትምህርት ቤት ጋር የሚገኙ ተጨባጭ ነገሮችን ማወቅ አለባቸው። ለምሳሌ ልጆች ወደ ትምህርት ቤት ምግብ ማምጣት እንደሚገባቸው ወተት እና ፍራ ፍሬ ትምህርት ቤት ውስጥ ሊገዛ እንደሚችል እንዲሁም የኖርዌይ ተማሪዎች ዩኒፎርም እንደማይለብሱ ማወቅ አለባቸው። ልጆቻቸው ትምህርት ከመጀመራቸው በፈት እንዴት ማስመዝገብ እንዳለባቸው ማወቅ ይኖርባቸዋል።

ወላጆች የኖርዌይ ሥርዓተ ትምህርት እና የት/ቤቶች ግምትን ማወቅ አስፈላጊ ነው። የኖርዌይ ት/ቤቶች በፊት እነሱ ይማሩባቸው ከነበሩ እና ከድሮ የለመዱት ት/ቤቶች የተለዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ የትምህርት አሰጣጥ እና የትምህርት ቤቶች ግቦችን ማወቃቸው አስፈላጊ ነው።

ት/ቤቶች ከወላጆች ምንድን የጠብቃሉ?

ቀዳሚው እና ዋናው አስፈላጊ ነገር ወላጆች ልጆቻቸው በትምህርት ረገድ ተነሳሽነት እንዲያሳዩ ነው። ተማሪዎች በትምህርት ገበታ፣ በትምህርት ነጥቦች ስለማይስጡ እና በአንድ የትምህርት ዘመን የሚደግም ተማሪ ስለሌለ አንድ አንድ ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያደርጉት ጥረት ብዙም አስፈላጊ አይደለም በማለት ሊያስቡ ይችላሉ። ይህንን አመለካከት ወደልጆቻቸው በመሸጋገር አመለካከታቸውን ሊያበላሹ ይችላሉ። ወላጆች ትምህርት አስፈላጊ እንደሆነ ለልጆቻቸው ማሳየት አለባቸው!

ወላጆች ለልጆቻቸው የቤት ሥራ እንደስሩ ሊያረጋግጡ ይገባል። ወላጆች የሚነበበውን ነገር በአጠቃላይ የማይረዱት ቢሆንም እንኳን ልጆቻቸው የሚነበብ የቤት ሥራ ሲኖራቸው ፀጥ ብለው ሊያዳምጧቸው መቻል አለባቸው። ወላጆች የትምህርት ቀን ከመጀመሩ በፊት ልጆቻቸው በቂ እንቅልፍ እና እረፍት እንዲያገኙ የማድረግ ኅላፊነት አለባቸው።

ከትምህርት ቤት ጋር መተባበር አስፈላጊ ነው። ት/ቤት ወላጆች ልጆቻቸውን የሚመለከት ስብሰባ ከመምህራን ጋር በሚኖርበት ጊዜ እንዲመጡ የሚጠብቅ ቢሆንም እንኳን ት/ቤት ግን ከዚህ በላይም ይጠብቃል። ወላጆች በክፍል ደረጃ ሊያደርጉት የሚችሉትን እንዲያደርጉ ለሕፃናቱ ሁሉም ልጆች አሳታፊ የሆኑ ስብሰባዎች ላይ እንዲያገኙ ይፈልጋል በት/ቤት ደረጃ እንዲሳተፉ እና በወላጆች የሥራ ኮሚቴ(FAU) አስተዋጽዎ ማበርከት ይችላሉ። በዚህ መንገድ ልጆቻቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ት/ቤቱ እንዲያግዛቸው በአቅም የዳበረ እንዲሆን ለማድረግ ወላጆች ማገዝ ይችላሉ። ወላጆች ልጆቻቸው የኖርዌጂያን ቋንቋ ከሚናገሩ ልጆች ጋር እንዲገናኙ እድል ሊሰጡ ይገባል። ይህ ግን ወላጆች ያገራቸውን ቋንቋ ችላ ማለት አለባቸው ማለት አይደለም። ልጆቹ ባላቸው የኖርዌጂያን ቋንቋ ችሎታ ልምምድ ማድረግ አለባቸው። በአገራቸው እንደሚያደርጉት የቃላት ልምምድ እና ሁኔታ በባሕላቸው ባሉት ልምዶች መሠረት ለልጆቻቸው ማንበብ ወይም መተረክ አለባቸው። ወላጆቻቸው ብቁ የሆኑ ትልልቅ ስዎች እንደሆኑ ልጆቻቸው ማወቃቸው ጠቃሚ ነው። አብዛኛው ጊዜ የትውልድ አገር ቋንቋቸውን ጥሩ አድርገው እስከሚችሉ ድረስ ይህ ነገር በበለጠ ተግባራዊ ይሆናል(ማለት የራሳቸው የሆነ)። የአገራቸውን ቋንቋ በጥሩ ሁኔታ የሚያውቁ ልጆች የኖርዌጂያን ቋንቋ በተሻለ ሁኔታ ይማራሉ።

ወላጆች ከት/ቤት ምንድን ይጠብቃሉ?

ልጆቻቸው ጥሩ ደረጃ ያለው እውቀት እንዲያገኙ ይጠብቃሉ። ብዙ ስደተኛ ወላጆች እነሱ እንደተማሩት ትምህርት አይነት ተመሳሳይ የሆነ ትምህርት እንዲኖር ይጠብቃሉ። መምህራን በትምህርት ክፍሎች ውስጥ ስርዓት እንዲኖር እንዲያደርጉ እና ለተማሪዎች እውቀት እንዲሰጡ ይጠብቃሉ። በኖርዌይ ትምህርት ቤቶች ሁኔታ በቀላሉ ተስፋ ሊቆርጡ ይችላሉ። ብዙዎች የዲሲፕሊን ገደብ እንደሌለ እና በጣም ከሥርዓት ውጭ እንደሆኑ ያስባሉ። የት/ቤት ግብ ልጆች በዘመናዊ የመረጃ ሕብረተሰብ ውስጥ ሆነው ራሳቸው የተማሩ ግለሰቦች እንዲሆኑ ያላቸውን አመለካከት ማሳደግ መሆኑን ያላወቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

ማንኛውም አይነት አለመግባባት አጋጥሞሽ ያውቃልን?

አንድ አንድ ወላጆች ከት/ቤት ግቢ ውጭ የሚሰጥ ትምህርት ከትምህርት ክፍሎች ውስጥ ከሚሰጠው ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አይረዱም። አንድ አንዶቹ ደግሞ ክፍል ትምህርታቸውን ወደ ደን በመሄድ መጎብኘት ሲሆን ልጆቻቸው ቤት ውስጥ እንዲቀሩ ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ትልቅ አለመግባባት ነው። ስለ ደን መጽሐፍ ውስጥ ያለውን ከማንበብ በላይ ወጣ በማድረግ ተፈጥሮን በማሳየት ስለ ተክሎች ማስተማር ይቀላል።

ለወደፊቱ እንዲሆኑ የምትጠብቂያቸው ተስፋዎችሽ ምንድን ናቸው?

ት/ቤቶችና እና ወላጆች የእየራሳቸውን ኅላፊነት እና ግዴታ እንዲረዱ እፈልጋለሁ። ሁለቱም አካላት ከተቻለ ተመሳሳይ የሆነ አክብሮት ሊኖራቸው ይገባል። በዚህም ሁለቱም በአንድ አይነት አቅጣጫ እንዲሄዱ እፈልጋለሁ። ይህም ለልጆች የተሻለ ነገር የሚፈጥር እንዲሁም እፈልጋለሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no