Intro
Amharisk • አማርኛ

ራጅንደሃር ካኡር

ኦስሎ ከተማ ውስጥ የምትኖር በሶንድረ ኖርድስትራንድ ዞን የምትሰራ የጤና ባላሙያ

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ስለ እራሳቸው ጤንነት እና ኖርዌይ ውስጥ የሚገኝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት በተመለከተ ማወቅ ያለባቸው አስፈላጊ ነገር ምንድን ነው?

ስደተኞች መደበኛ የሕክምና እርዳታን በተመለከተ ማወቅ አለባቸው። እራሳቸው መደበኛ ሀኪም ማግኘት እንዳለባቸው ማወቅ ይገባቸዋል። እድሜያቸው ከ6 ዓመት በታች የሆኑ ልጆች በአካባቢያቸው በሚገኝ ክሊኒክ ወይም የዞን አስተዳደር መጠየቅ ይገባል። ስለዚህ ሕፃኑ በክሊኒክ ሕዝባዊ ጤንነት የተመዘገበ ይሆናል። እንደ መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ ሕዝባዊ ጤና ክሊኒኮች እና በዞን ወይም በአስተዳደር የሚገኙ ሕፃናትን በተመለከተ መረጃ ስለማይኖራቸው ብዙ ልጆች ከዚህ የእርዳታ ሥራዓት ውጭ ይሆናሉ። ወላጆች ከሕዝባዊ ጤና ክሊኒክ በሚደረግ ቀጠሮ መገኘት አለባቸው ወይም በቅያሪ ሌሎች እንዲመዘግቧቸው ማድረግ አለባቸው። ያለምክኒያት ለብዙ ጊዜ መቅረት ግን የሕፃናት ጤና አገልግሎት እንዲቀርባቸው ያደርጋል። ብዙ ሰዎች ሲታመሙ ብቻ ወደ ሐኪም የመሄድ ልምድ ስላላቸው ለምርመራ በማለት መሄድ አልተለመደም።

ስደተኞች ወደዚህ ቦታ መሄድ ብቻ ሳይሆን በሃኪም ወይም በሕዝባዊ ጤና ክሊኒክ ለመታየት እራሳችሁ ቀጠሮ መያዝ እንደሚገባችሁ ማወቅ አለባችሁ። ሁኔታው አደገኛ ካልሆነ በተመሳሳይ ቀን ቀጠሮ መገኘት አይጠበቅባቸውም። አንድ ሰው በተስማማበት የቀጠሮ ቀን በአካል ካልተገኘ እና ለምን እንደቀረም መልእክት ሳይሰጥ ከቀረ ለቀጠሮ ገንዘብ መክፈል አለበት።

አገራዊ የጤና አገልግሎት ከስደተኞች ምንድን ይጠብቃል?

ስደተኞች አገራዊ የጤና አገልግሎት ኖርዌይ ውስጥ እንዴት እንደሚሰራ ማወቅ እና በተስማሙበት መልኩ ከሀኪሞች ወይም የሕዝባዊ ጤና ክሊኒኮች በያዙት ቀጠሮ በአካል መገኘት አለባቸው።

ስደተኞች ከአገራዊ የጤና አገልግሎት ምንድን ይጠብቃል?

እራሳቸው እና ልጆቻቸውን በተገቢው መልኩ ክትትል እንዲደረግላቸው እና እንዲታከሙ ይጠብቃሉ። እንዲሁም በአክብሮት መታከም ይጠብቃሉ።

አንድ አንዴ ስደተኞች ከብሔራዊ ጤና አገልግሎት ለማግኘት የሚጠብቁት ተጨባጭ ያልሆነ አክብሮት እንዳለ አውቃለሁ። ለምሳሌ አንድ ስው አካል ጉዳተኛ ልጅ ሲኖረው መብቶችን እና ሊያገኘው ስለሚችል ሕክምና ምንነት ማወቅ ያለበት ብዙ ነገሮች አሉ።

ብዙ ስደተኞች ለቀላል ችግሮች ለምሳሌ ለጉንፋን እና ለመሳሰሉት ሕክምና ለማግኘት ወደ ሃኪም ይመጣሉ። ሃኪሙ ደግሞ መዳኒት ሳይሰጥ ገንዘብ ሊያስከፍላቸው ይችላል። ይህም ሃኪም መጥፎ ሥራ እንደሰራ ያስባሉ።

ማንኛውም አይነት አለምግባባት አጋጥሞዎት ያውቃልን?

ወደ ኖርዌይ ለመጀመሪያ በመጣሁበት ጊዜ ያጋጠመኝን በደንብ አስታውሳለሁ። ከባለቤቴ ውጭ ሌላ ቤተሰብ አልነበረንም። የመጀመሪያ ልጃችንን እርጉዝ ነበርኩ። ያጥወለውለኝ፣ ያስታውከኝ እና ጥሩ ስሜት አይሰማኝም ነበር። ወደ ሥራ ጭራሽ መሄድ እንደማልችል ተሰማኝ። ወደ ሃኪም በመሄድ የህክምና የምስክር ወረቀት እንዲሰጡኝ ጠየኳቸው። ስለታመምኩ ሳይሆን እርጉዝ እንደሆንኩ ተነገረኝ። እንድ አዋላጅ የሆነች ሴት፣ የህክምና የምስክር ወረቀት እንዳትሰጧት ሰነፍ ስለሆነች ነው በማለት ስትናገር ሰማኋት። ያኔ የሚረዳኝ ስው እንደሌለ በጣም ተሰማኝ። ከሥራ በመቅረት ቤት ለመዋል እነሱን ለማታለል በመሞከር እንደ ተዋረድኩ እና እንደተጠረጠርኩ ተሰማኝ። በጣም አስፈላጊ ነው ሰዎች በአክብሮት መያዝ አንዳለባቸው።

ሌላው ነገር አንድ አንድ ወላጅ ችግራቸው በተመለከተ ከእኔ ጋር መነጋገር አስቸጋሪ ሆኖ ያገኙታል። ይህ ግን በእውነት አለመግባባት ነው ወይስ አይደለም የሚለውን አላቅም። ለምሳሌ የቤተሰባቸው ገቢ ዝቅተኛ መሆኑን የማይነግሩኝ ከሆነ ድፍረት ሊያጡ ይችላሉ። ይህ ማለት ይህንን ነገር በቀላሉ ሊነጋገሩበት ስለማይችሉ ልጆቻቸውን ወደ መዋለ ህፃናት እንዲያስገቡ ሃሳብ ስሰጣቸው ሳይቃወሙ እሺ በማለት ይመልሱልኛል። ኋላ ግን ህፃኑ ትምህርት ሳይጀምር ሲቀር ወላጆች እሺ ያሉትን ለመፈጸም አልተጨነቁበትም በማለት ላስብ እችላለሁ።

ለወደፊቱ እንዲሆኑ የምትጠብቋቸው ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

ለአካለ መጠን የደረሱ ስደተኞች የሚጠቀሙበት የተለየ ሕዝባዊ የጤና ኪሊኒክ ማየት እፈልጋለሁ። የተለያዩ የቡድን ውይይት የሚደረግበት መገናኛ ቦታ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል። ወላጆችን፣ አመጋገብ ሥርአት፣ አኗኗር ጤና እና ሌሎችን እነሱን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ የምክር አገልግሎት በመስጠት ሥራ መሥራት እንችላለን። ዋናው የሚያተኩረው ደህንነት ላይ ይሆናል። አንድ ሰው ቀላል የሆነ ስቃይ ጋር ሊኖር እንደሚችል የሆነ ሆኖ ሁል ጊዜ ችግር ሳይገጥመው ጥሩ ሕይወት፣ ፍጹም የሆነ ደህንነት እና የደስታ ኑሮ ሊኖር እንደሚችል ማወቅ አለበት ብዬ አስባለሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no