Intro
Amharisk • አማርኛ

አፍሻን ራፊቅ

የቀድሞ አቃባዊ ፓርቲ (Høyre(H)) ወኪል በስቶርቲንጌ

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ስለ ኖርዌይ ሕብረተሰብ ሊያወቁ የሚገባቸው አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ፈጣን እና ቀላል የሆነ የኖርዌይ ታሪክ፣ ፖለቲካዊ ሥርዓት ሕጎች እና መመሪያዎች እንዲሁም በኖርዌይ በመኖራቸው ያለባቸውን ግዴታዎች እና መብቶች ምን እንደሆኑ ማወቅ አለበቸው።

የኖርዌይ ሕብረተሰብ ከስደተኞች ምን ይጠብቃል?

የኖርዌይ ሕጎችን እና መመሪያዎችን ተግባራዊ እንዲያደርጉ የኖርዌይ ቋንቋ እንዲማሩ እንዲሁም ከኖርዌይ ሕብረተሰብ ጋር እንዲዋሕዱ ነው።

ስደተኞች ከኖርዌይ ሕብረተሰብ ምን ይጠብቃሉ?

ስደተኞች ባህላቸው እና ማንነታቸው እንዲጠበቅ ይጠብቃሉ። ባላቸው ልዩነት ዙሪያ የጋራ መከባበር መግባባት እና መቻቻል እንዲኖር ይጠብቃሉ። አብዛኞቹ ሥራ ለማግኘት እና በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሳቸውን ለመቻል የሚፈልጉ ቢሆንም እንኳን በገበያ ውስጥ ግን አድሎ/ልዪነት ያጋጥማቸዋል።

እኔ በተለይ የማተኩርበት ጉዳይ አድሎ እንዲሁም ተከትሎ የሚከሰት የውሕደት እጥረት ላይ ነው። በዘር የኋላ ማንነታቸው አተነሳ የሆኑ ብዙ ሰዎች ባለው የስራ ገበያ አድሎ እንደሚያጋጥማቸው እናውቃለን። ሥራ በማግኘት ረገድ ችግር እንዳጋጠማቸው እና ሥራ ያገኙ ብዙ ሰዎች ባላቸው ብቃት ችሎታ አስተዋጽዎ ለማድረግ ያላቸው ፍላጎት እና ፈቃድ የማይስማማ አነስተኛ የሥራ ተሞክሮ ምስክርነት ተቀባይነት በማግኘት እና በዚህ አገር የሥራ ልምድ በማቅረብ ችግር ያጋጥማቸዋል። ውጤታማ የሆነ የምስክር ወረቀት ደረጃ ሥርዓት በማቋቋም የመሥራት ፍላጎት አለኝ በዚህም ብቁ ሰዎች ከችሎታቸው እና ከብቃታቸው ጋር የሚመጣጠን ሥራ ማግኘት ይችላሉ። ስራ ውጤታማ የሆነ ውሁደት እንዲኖር መፍቴ መሆኑ ሁሉም ስው ይስማማል። ሁሉም ሰው እራሱን እና ቤተሰቡን ሌላ እድል እንዲያገኝ በእውነት ወሳኝ ነው። ስለዚህ ሁሉም የተሟሉ የኖርዌይ ሕብረተሰብ አባላት መሆን ይችላሉ።

ብዙ የንግድ ድርጅቶች ብዙ ስራተኛ እንደሚፈልጉ የታወቀ ጉዳይ ነው። በተመሳሳይ የዘር ማንነታቸው ምክኒያት አናሳ የሆኑ ብዙ ሰዎች ሥራ በማግኘት ረገድ ችግር አለባቸው። እነዚህን ሁኔታዎች ግምት ውስጥ በማስገባት የውጭ አገር ስም ያላቸው ሥራ ፈላጊዎች ኖርዌይ ውስጥ ያገኙት ትምህርት እሃ የሥራ ልምድ ቢኖራቸውም ወይም አስፈላጊ የብቃት መስፈርት የሚያሟሉ ቢሆንም ለሥራ ውድድር ቃለ መጥይቅ አይጠሩም። ይህ ደግሞ የኖርዌይ ሕብረተሰብን የማይጠቅም የሰባዊ አቅም ብክነት ነው። በመንገድ ሥራ አስተዋጽዎ ለማድረግ የሚፈልጉ ብዙ ስዎች ወደ ሥራ ገበያ ለመግባት የሚያስገባቸው ሁኔታ በቀላሉ ለማግኘት መንገዶች ማግኘት ነው። ቀላል የሚባል መፍትሄ የለም። በጣም አስፈላጊው ነገር በመንግስት እቅዶች እና የንግድ ድርድቶች መካከል ውደት መፍጠር ነው። የኖርዌይ ምሳሌ እንደሚለው የሚስማሙ ልጆች አንድ ላይ ሆነው የበለጠ ጨዋታ ይጫወታሉ እንደሚባለው አብዛኞቹ ኖርዌጂያዊያን አሰሪዎች ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ንቁ ተሳትፎ ማድረግ አለባቸው። እዚህ ላይ ሊታይ የሚገባው የአመልካቹ የዘር ማንነት ሳይሆን ግለሰቡ ለሚያመለክተው ሥራ ብቁ ነው ወይስ አይደለም የሚለው ጉዳይ ነው።

ማንኛውም አይነት አለመግባባት አጋጥሞሽ ያውቃልን?

አላጋጠመኝም፣ እዚህ ስለተወለድኩ እና ኖርዌይ ውስጥ ስላደጉ ይህንን ሕብረተሰብ በደንብ አውቀዋለሁ እንዲሁም የኖርዌይ ቋንቋን ሙሉ በሙሉ አቃለሁ ብዬ አስባለሁ። ይህ ደግሞ አለመግባባት የመፈጠር ሁኔታ እንዲቀንስ ይረዳል።

ለወደፊቱ እንዲሆኑ የምትጠብቂያቸው ተስፋዎችሽ ምንድን ናቸው?

ሁሉም ሰው ከሌሎች የተለየ ሰው ሆኖ የሚኖርበት መብት የሚያገኝበት ሕብረተሰብ የማየት ፍላጎት አለኝ። የዘር የኋላ ማንነቱ ምንም ሆነ ምንም ሁሉም ሰው ያለውን አቅም ለመጠቀም ማለትም ሥራ ለማግኘት፣ እራሱን ችሎ የሚኖር ሰው ለመሆን፣ እራሱን እና ቤተሰቡን ለመርዳት አንድ አይነት እድል ሊኖረው ይገባል። በጣም አስፈላጊው ነጥብ ስዎች ማናቸው ወይም የዘር ማንነታቸው ምንድን ነው ሳይባል ያላቸው ብቃት እና ልዩነት ክብር እንዲያገኝ አንድ አይነት መብት ያላቸው ግለሰቦች ሆነው መያዝ አለባቸው።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no