Intro
Amharisk • አማርኛ

ሳዲ ኤመቺ

የግራ ሰልፍ ወኪል (Representative of the Socialist Left Party) እንዲሁም የድራመን ከተማ አስተዳደር ሚክር ቤት አባል

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ስለ ኖርዌይ ሕብረተሰብ ሊያወቅ የሚገባቸው አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?

ስደተኞች ኖርዌጂያዊያን ከሀይማኖት ጋር ያላቸውን ዝምድና በተመለከተ ያለውን ነገር ማወቅ አለባቸው። በኖርዌይ የሚያዩትን ሁሉንም ነገር በክርስትና እምነት ተቀባይነት ያለው ሊሆን እንደማይችል ሊረዱ ይገባል። ለምሳሌ ብዙዎች ስደተኞች የሰከሩ ኖርዌጂያዊያን በቅዳሜና እሁድ መንገድ ላይ ያያሉ። ስለዚው ሁሉም ኖርዌጂያዊያን ይጠጣሉ። ይህ ደግሞ በክርስትና የተለመደ ሕይወት ነው በማለት ያስባሉ። ነገር ግን እውነታው እንደዚህ አይደለም። በሌሎች አገሮች እንዳለ ሀይማኖት ሁሉ በዚህ አገር ህብረተሰብ ይህ ነገር የታወቀ እንዳልሆነ መታወቅ አለበት። አብዛኞቹ ኖርዌዊጃዊያን ደግሞ ሀይማኖተኞች አይደሉም።

ሌላ ደግሞ ስደተኞች ለአብዛኛው ኖርዌጂያዊያን ከማይወክሉ ኖርዌጂያዊያን ሰዎች ጋር ይገናኛሉ። እንደመጥፎ አጋጣሚ ሆኖ ወጣት ስደተኞች ችግር ካለባቸው ወጣት ኖርዌጂያዊያን ጋር ብዙውን ጊዜ አንድ ላይ ያሳልፋሉ። ይህ ደግሞ ኖርዌጂያዊያን ልክ እንደሚያገኟቸው ወጣቶች እና ቤተሰቦች ናቸው በማለት እንዲያምኑ ያደርጓቸዋል።

ኖርዌጂያዊያን ውስጥ የሚገኙ ስደተኞች ስለ ኖርዌጂያዊያን አኗኗር እና ባህል ለመማር ተነሳሽነት ሊኖራቸው ይገባል ብዬ አምናለሁ። የእየሱስ ክርስቶስ ልደት እና ትንሳኤን በተመለከተ ተምረው በእነዚህ በአላት አክብሮት ሊያሳዩ ይገባል። ስደተኞች ኖርዌጂያዊያን እነማን መሆናቸውን ለማወቅ መጀመሪያ አጠቃላይ አካሄዳቸውን ሊረዱ እና በልማድ የተቀመጡ/ያልተፃፉ ሕጎችን መማር ወይም ማወቅ አለባቸው። ይህ ደግሞ ከኖርዌጂያዊያን ጋር በሚገናኙበት ወቅት በበለጠ በራስ መተማመን ያላቸው እንደሆኑ ያደርጋቸዋል።

የኖርዌይ ሕብረተሰብ ከስደተኞች ምን ይጠብቃል?

የኖርዌይ ሕብረተሰብ እዚህ ከሚኖር እያንዳንዱ ሰው ብዙ ነገር ይጠብቃል። ይህ ደግሞ ለስደተኞች እና ለኖርዌጂያዊያኖች እኩል የሚመለከት ነው። ሕጎችን እና መመሪያዎችን አውቀን ተግባራዊ እንድናደርግ ሕብረተሰቡ ይጠብቃል። የዳበረ ሕብረተሰብ ብዙ ነገሮች እንዲፈፀሙ ግድ ይላል። በትምሕርት እና ሥራ ረገድ በእኩል ውጤታማ እንዲሆን ይጠበቅብናል። ቤተሰባችን ውጤታማ እንዲሆን ይጠበቅበታል። ለልጆቻችን ጥበቃ እንድናደርግላቸው ይጠበቅበታል። እነዚህን ግምቶች ተግባራዊ ማድረግ ያልቻሉ ባለው አጠቃላይ አካሄድ በቀላሉ ወደኋላ ሊቀሩ ይችላሉ።

ሕብረተሰቡ ተጨባጭ ያልሆነ አንድ አንድ ነገሮችን እንዲያደርጉ ለአንድ አንድ ስደተኞችን ይጠይቃሉ። ኖርዌጂያዊያን ከ60 ዓመታት በፊት የበቃ ጦርነትን በተመለከተ እስከ አሁን ድረስ ማውራት ያልተው ሰዎች አሉ። ያለፈ ጊዜ ቁስል ያላቸው ስደተኞች ደግሞ ያጋጠማቸውን መጥፎ ነገር በፍጥነት ወደኋላ መተው እንዲችሉ አይጠበቅባቸውም።

ስደተኞች ከኖርዌይ ሕብረተሰብ ምን ይጠብቃሉ?

እኔ እንደማምነው በፊት የስደተኞች ግምት ጥሩ ነበር። በ1980ዎቹ ብዙ ስደተኞች ሕብረተሰቡ የእነርሱን ችግር እንዲፈታ ይጠብቁ ነበር። ግን በአሁኑ ሰዓት እንዲ አይነት ግሚቶች መኖራቸውን እርግጠኛ አይደለሁም። አብዛኛው ጊዜ ይህ ግምት ግን እውነት ነው። በተናጥል የኋላ ማንነት እያንዳንዱ ስደተኞች የተለያየ ማንነት አለው።

ማንኛውም አይነት አለምግባባት አጋጥሞዎት ያውቃልን?

ስደተኞች አብዛኛው ጊዜ የሚያገኙት መረጃ ከአገራቸው ልጅ የሚያገኙት መሆኑ ይታወቃል። ይህ መረጃ ብዙውን ጊዜ ቀና ያልሆነ እና አለመግባባትን የሚፈጥር ነው። እነዚህን አለመግባባቶች መፍታት ከባድ ነው።

ለወደፊቱ ሊሆኑ ይችላሉ በማለት የምትጠብቃቸው ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

ስደተኞች ሕብረተሰብ ውስጥ በብዛት ካልተሳተፉ እና ካልሰሩ እነዚህ ስደተኞች በኖርዌይ ዝቅተኛ የሕዝብ ክፍል እንዳይሆኑ ፍርሃት አለኝ።

ስደተኞች በኖርዌይ ሕብረተሰብ ውስጥ በተሻለ ብቃት እንዲሳተፉ ፍላጎት አለኝ። ባሉበት ማሕበረሰብ ለምሳሌ በረዳኤት ኮሚቴዎች እንዲሁም ከኖርዌጂያዊያን በጋራ በመሆን በሕዝባዊ ሥራዎች በመሳተፍ ውጤታማ ሆነው እንዲታዩ ይፈልጋሉ።

ሁሉም ወጣቶች በራሳቸው መነሻ የኋላ ማንነት እንዲሁም በኖዌጂያዊነታቸው ኩሩዎች ከሆኑ እንዴት ጥሩ እንደሚሆን አስቡት።

አንድ ቱርካዊ በድራመን ጎዳናዎች አግኝቼ «ከየት ነህ የመጣኸው» ብዬ ስጠይቀው «ከድራመን ነኝ» በማለት ሲመልስልኝ ለመስማት እፈልጋለሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no