Intro
Amharisk • አማርኛ

መርሲሃ ሰሂክ

በትሮንድሃይም የከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኝ ለስደተኞች ብቁነት ማእከል የሚሰራ አማካሪ ፕሮግራም (Qualification Centre for Immigrants)

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ አዳዲስ ስደተኞች ስለ ኖርዌይ ሕብረተሰብ ሊያወቁ የሚገባቸው አስፈላጊ ነገሮች ምንድን ናቸው?

በጣም የዳበረ ሕጋዊ ቁጥጥር በሚደረግበት ዲሞክራሳዊ ሕብረተሰብ ውስጥ የምንኖር መሆናችንን ስደተኞች ማወቃቸው አስፈላጊ ነው ብዬ አስባለው። ኖርዌይ ጥሩ እና ለነዋሪዎቿ የምትመች አስተማማኝ አገር ናት። የግብር ክፍያ ለእኛ ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ሰው ጥቅም ይስጣል።

ስደተኞች በዚህ አገር ስላላቸው የትምህርት እድሎች ሊያውቁ ይገባል። ይዘውት የሚመጡት ችሎታን እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው። ስደተኞች ጥቂት ጊዜ ከቆዪ በኋላ ሥራ ሊጀምሩ ይገባል። ስለዚህ እራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን መደገፍ ይችላሉ።

ኖርዌይ ውስጥ ስኬታማ ለመሆን የግንኙነት መረቦችን ማሳደግ አስፈላጊ ነው። ስለ ኖርዌጂያዊያን ስንናገር እስፓርት እና ከቤት ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ለብዙ ስዎች አስፈላጊ መሆናቸው ወላጆች ለጊዜ ማሳለፊያነት የሚደረጉ ብዙ ተግባራት ውስጥ ከልጆቻቸው ጋር እንደሚሄዱ እና ቀጠሮን ማክበር ጥሩ ባሕሪ እንደሆነ ስደተኞች ሊያውቁ ይገባል።

እንደ አማካሪነትዎ በመሠረታዊ ፕሮግራም (introduction programme) ውስጥ ከሚሳተፉት ስደተኞች ምን ይጠብቃሉ?

አዲስ የሚመጡ ስደተኞች እራሳቸውን በማዘጋጀት ውጥን ፕሮግራም ውስጥ በብቃት እንዲሳተፉ እና በሚያደርጉት ተሳትፎ ሃሳባቸውን እንዲሳጡ ይጠበቅባቸዋል። መሰረታዊ ፕሮግራም በግል ውጤታማ ለመሆን በሚያደርጉት የመጀመሪያውን ጥረት አጋዥ እንደሆነ እንደሚረዱ ተስፋ አደርጋለሁ። በመሰረታዊ ወይም በመግባቢያ ፕሮግራም ውስጥ የሚሳተፍ እያንዳንዱ ተሳታፊ ከሌላ ሰው የተለየ ስለሆነ ሊያሳድገው የሚችል የችሎታ አይነትን ይጎናፀፋል። የኖርዌጂያን ቋንቋ በኖርዌይ ሕብረተሰብ ውስጥ ብዙ መግቢያዎችን የሚከፍት ቁልፍ ነው። ስደተኞች በተመደበላቸው የአማካሪዎች ፕሮግራም ውስጥ በሚወያዪበት ወቅት እራሳቸው የሚኒሳሱ ግልጽ ከሆኑ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

ስደተኞች ከመሰረታዊ ፕሮግራም ምን ይጠብቃሉ?

ጥሩ በሆነ መንገድ እንዲያዙ እና መሠረታዊ ፕሮግራም ደግሞ የፊይናንስ ዋስትና እንዲስጣቸው ይጠብቃሉ። ብዙዎቹ ስደተኞች መሠረታዊ ፕሮግራም ከኖርዌጂያውያን ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት እንዲያቃልላቸው ይጠብቃሉ። ስለ ገበያ ስራ እና ያሉበት ማህበረስብ በተመለከተ መረጃ እናገኛለን ብለው ይጠብቃሉ። ብዞዎቹ ከትምህርት ሰዓት ውጭ በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ መሳተፍ ይፈልጋሉ።

ማንኛውም አይነት አለምግባባት አጋጥሞዎት ያውቃልን?

ስደተኞች ተራ የአማካሪ ፕሮግራምን በሥሕተት ይገነዘቡታል። መሠረታዊ ፕሮግራም በሚጀመርበት ጊዜ ተሳታፊ የሆነ ተጨባጭ ነገሮች የሚገኙበት ብዙ እገዛ ይቀበላል። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ግን ስደተኛው እራሱ ወይም እራሷ ብዙ ነገር ማድረግ እንዲችሉ ይጠበቅባቸዋል።

ለወደፊቱ እንዲሆኑ የምትጠብቋቸው ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

በመሠረታዊ ፕሮግራም ውስጥ የሚገኙ ተሳታፊዎች ባሏቸው የተለያዩ ዓይነት ችሎታዎች እንዲሰሩበት እንዲሁም መሠረታዊ ፕሮግራሙ እና ሕብረተሰብ በሚስጣቸው እድሎች እንደሚጠቀሙበት ተስፋ አደርጋለሁ። በተጨማሪም የሚሰጠው ፕሮግራም ጠቃሚ መሆኑ ታውቆ እያድንዳንዱ ሰው ስኬታማ እንዲሆን እርዳታ ያደርጋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ስኬታማ የሆነ ውሕደት እንዲኖር ስደተኞችን ያጠቃለለ የተናጠል ኃላፊነት አለባቸው። ስለዚህ በዚህ ፕሮግራም የሚሳተፉ ሁሉም ሰዎች የራሳቸው የግል እቅድ በመንደፍ ረገድ እንዲሳተፉ እን ድርሻቸውን መወጣታቸው አስፈላጊ ነው። የንግድ ዘርፎች እና የመንግስት አካላት እስከ አሁን ድረስ ካላቸው በበለጠ ደረጃ ከኖርዌጂያዊያን የሚለይ የኋላ ማንነት ያላቸው ሰዎችን መቅጠር አለባቸው።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no