Intro
Amharisk • አማርኛ

ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ የታወቁ እንስሳት

ኖርዌይ የብዙ የዱር እንስሳት መኖርያ አገር ናት። የኖርዌይ አብዛኞቹ እንስሳት ለሰው ልጅ አደገኛ አይደሉም። የዱር እንስሳትን ሳንፈራ የገጠር ቦታዎችን ተጠንቅቀን ልንጠቀምባቸው እንችላለን። አንዳንዶቹ እንስሳት ጫካ ውስጥ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ ተራሮች ላይ ይኖራሉ።

ከነዚህ መካከል በደንበኛ የምንመለከታቸው፦

 • ድብ
 • ሽኮኮ(ምፅፁላይ)
 • ትልቅ አጋዘን (ኤልክ)
 • ነብር የሚመስል ትልቅ ድመት
 • ጥንቸል
 • አጋዘን (ዲር)
 • ረይን አጋዘን (ረይንዲር)
 • ሮ አጋዘን (ሮ-ዲር)
 • ቀበሮ
 • ተኩላ
 • እፍኝት (እባብ)

©Baard Næss/Samfoto©Baard Næss/Samfoto

ድብ

በኖርዌይ ውስጥ የተለያዩ የድብ አይነቶች ይገኛሉ። በዋናው መሬት (mainland) ውስጥ የሚገኝ የድብ አይነት ቡና አይነት ድብ ተብሎ ይጠራል። በአሁኑ ጊዜ በኖርዌይ ጫካዎች ውስጥ ብዛት ያላቸው ቡና አይነት ድቦች አናገኝም። ቡና አይነት ድብ እስከ ጅራቱ ድረስ 125 ሴ.ሜ የሚደርስ ርዝመት አለው። ክብደቱ ደግሞ 350ኪ.ግ ሊደርስ ይችላል። በዋነኝነት የቤት ፍሬዎችንና አትክልቶችን የሚመገብ ቢሆንም እንኳ አልፎ አልፎ በጎችን ሊበላ ይችላል።

ድብ ሙሉውን የበጋ ወቅት ተኝተው ያሳልፋሉ። መኖሪያቸው የተቆፈረ ጉድጓድ ወይም ዋሻዎች ሊሆን ይችላል። ፀደይ/አየት እስከሚመጣ በዚህ ቦታ ይገኛሉ።


©Asgeir Helgestad/Samfoto©Asgeir Helgestad/Samfoto

ሽኮኮ(ምጽጹላይ)

ይህ እንስሳ በመላ አገሪቱ ሊገኝ የሚችል ቢሆንም እንኳን ጥድ በሞላባችው ደኖች ውስጥ በብዛት ይገኛል። እንስሳው ረጅም እና ጸጉራም በሆነው ጭራው በቀላሉ ይታወቃል። ጸጉሩ በክረምት ወቅት ወደ ቀይ የሆደ ቡና አይነት ይሆናል። በበጋ ወቅት ወደ አመድማ ነጭ ይሆናል። ይህ ሽኮኮ ፍራ ፍሬ እና ተክሎች የሚመገብ ቢሆንም እንኳን ጫጩቶችን እና የአእዋፍ እንቁላል ለበላ ይችላል። ክብደቱ አንድ ኪሎ ግራም አካባቢ ይመዝናል።


©Kjell-Erik Moseid/Samfoto©Kjell-Erik Moseid/Samfoto

ትልቅ የአጋዘን አይነት (ኢልግ)

ትልቅ የአጋዘን አይነት /ኢልክ በኖርዌይ ጫካዎች ውስጥ ከሚገኙ ትልቅ እንስሳ ነው። አብዛኛው ጊዜ የጫካ ንጉስ ተብሎ ይጠራል። የወንድ አጋዘን/ኢልግ ቀንድ ቅርንጫፍ ያለው ሆኖ ቁመቱ 150ሴ.ሜ በላይ ሊሆን ይችላል። አንድ ትልቅ አጋዘን /ኢልግ እስከ ወገቡ ድረስ ያለውን ቁመት 130 ሴ.ሜ ሊሆን የሚችል ሲሆን ሚዛኑ ደግሞ ከ400 እስከ 800 ኪሎ ግራም ሊደርስ ይችላል። ይህ እንሰሳ ቅጠይ(ሳር) በል ነው።


©Asle Hjellbrekke/Samfoto©Asle Hjellbrekke/Samfoto

ጭኳ አንበሳ(ነብር የሚመስል ትልቅ ድመት)

ይህ እንሰሳ ግዙፍ የቤት ድመትን የሚመስል ሲሆን ጆሮ አካባቢ ጥቁር ቀለም ያለው ጠቃ ጠቆ አለው። ይህ እንሰሳ በጣም ጥቁር ቀለም ነጠብጣብ ያለው ቡና ቀለም ኖሮት የጭራው ጫፍ ጥቁር ነው። ትሮምስ እስከሚባለው ሰሜናዊ የአገሪቱ ክፍል ድረስ በመላ አገሪቱ የሚገኙ ጫካዎች ውስጥ ይኖራል። አብዛኛውን ጊዜ ቁመቱ 1 ሜትር አካባቢ ይሆናል። አዳኝ እንስሳ በመሆኑ ወፎችን ጥንቸሎን እና ትንንሽ እንስሳትን ይመገባል። እንዲሁም ድመቶችን እና በጎችን ሊበላ ይችላል።


©Steinar Myhr/Samfoto©Steinar Myhr/Samfoto

ጥንቸል

በመላው ዓለም ወደ 100 የሚደርሱት የጥንቸል ዝርያ አይነቶች አሉ። ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙት ጥንቸሎች ቁመታቸው እስከ 60 ሴ.ሜ ይደርሳል። ጥንቸሎች ትልቅ የላይ የፊት ጥርስ ረዥም እና ሃይለኛ እግሮች አጭር ጭራ እና ረዥም ጆሮዎች አሏቸው። የጥንቸል ፀጉር እንደየወቅቱ ቀለሙ ይቀያየራል። በክረምት ወደ አመድማ ያዘነበለ ቡና አይነት ሲሆን በበጋ ወቅት ነጭ ይሆናል። ጥንቸሎች በመላው አገሪቱ ሊገኙ የሚችሉ ቢሆኑም እንኳን በጫካዎች ለጥ ባሉ ቦታዎች በገጠር እና በተራሮች በብዛት ይገኛሉ። ጥንቸል ሳር በል እንስሳ ነው።


©Helge Sunde/Samfoto©Helge Sunde/Samfoto

አጋዘን (ዲር)

አጋዘን (ዲር) በኖርዌይ ሁሉም ጫካዎችና የደን ዳርቻዎች ሊገኙ ይችላሉ። ፀጉራቸው በክረምት ወቅት ቀይ አመድማ ወይም ቡና አይነት ሲሆን በበጋ ወቅት በጣም ጥቁር እና አመድማ ይሆናል። አጋዘን (ዲር) ሳር በል ሆነው እስከ ወገባቸው ያለው ቁመት 125 ሴ.ሜ ይደርሳል። ወንድ አጋዘን የሚያስገርም ቅርንጫፍ ያለው ቀንድ አላቸው። ወንድ አጋዘን (ሮያል ስታግ) ጫካ ውስጥ ከሚኖሩ በጣም የተዋበ መልክ ካላቸው እንስሳት ይመደባል።


©Tom Schandy/Samfoto©Tom Schandy/Samfoto

ረይን አጋዘን (ሬይን ዲር)

ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ አብዛኞቹ ረይን አጋዘኖች የቤት እንስሳት ሆነው የሚራቡ ናቸው። የዱር ረይን አጋዘን ደግሞ ስቫልባርድ እንዲሁም በደቡብ ተራሮች ሐርዳን ገርቪዳ፣ ዶቭረ እና ሮንዳነ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። ረይን አጋዘን የሚመደበው ከአጋዘን ዘር ነው። ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ ረይን አጋዘኖች ግዙፍ አይደሉም። ትልቅ ረይን አጋዘን አብዛኛው ጊዜ ቁመቱ ከ107 ሴ.ሜ እስከ 127 ሴ.ሜ ይደርሳል። ወንድ እና ሴት ኖርዌይ ረይን አጋዘኖች ቅርንጫፍ ያለው ቀንድ አላቸው። ረይን አጋዘን ሳር በል እንስሳ ናቸው።


©Kjell-Erik Moseid/Samfoto©Kjell-Erik Moseid/Samfoto

ሮ አጋዘን (ሮ ዲር)

በፊት ሮ አጋዘን በኖርዌይ ምስራቃዊ ጫካዎች እና ደኖች ውስጥ ብቻ ሊገኙ የሚችሉ ነበሩ። በአሁኑ ወቅት ግን በመለው አገሪቱ ተሰራጭተው ይገኛሉ። ሮ አጋዘን ክአጋዘን ዘር ይመደባል። ወንድ ሮ አጋዘን ቀንዱ ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን አንድ ትልቅ ሮ አጋዘን ቁመቱ ከ64 እስከ 89 ሴ.ሜ ሊደርስ ይችላል። ክብደቱ ደግሞ ከ17 እስከ 23 ኪሎ ግራም ብቻ ይመዝናል። ሮ አጋዘን ሳር በል እንስሳ ነው።


©Baard Næss/Samfoto©Baard Næss/Samfoto

ቀበሮ

በመላው ዓለም 20 ዓይነት የተለያዩ የቀበሮ ዝርያዎች አሉ። ኖርዌይ ውስጥ የሚገኘው በጣም የታወቀው ቀበሮ ቀይ ቀበሮ ነው። ጫካዎች ውስጥ በሚገኝ የአራዊቶች መኖሪያ ይኖራል የአራዊት ሰፈር ከመሬት በታች የተቆፈረ ጉድጓድ ነው። ይህ ቀበሮ 75 ሴ.ሜ ድረስ ቁመት ይኖረዋል እስከ 50 ሴ.ሜ እርዝመት ያለው የሚያስገርም ረዥም ጭራ አለው። የቀበሮ ፀጉር ወደ ቀይ ያደላ ቡና አይነት ሲሆን ሆዱ እና የጭራው ጫፍ ደግሞ ነጭ ነው። እንስሳው አዳኝ ሲሆን አይጥ ጥንቸል አዋፍን እና ዓሳን ይመገባል። እንዲሁም የጫካ ፍሬ ቤሪ ይመገባል።


©Baard Næss/Samfoto©Baard Næss/Samfoto

ተኩላ

ተኩላ ከውሻ ዘር የሚመደብ ሲሆን ቡና አይነት ነጠብጣብ አለው። ሆዱ ነጭ ቀለም አለው። ተኩላ የመጥፋት አደጋ የተጋጠመበት ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ቁጥራቸው ትንሽ የሆኑ ተኩላዎች ብቻ ኖርዌይ ዉስጥ ይገኛሉ። ተኩላ አብዛኛውን ጊዜ በቡድን ከ6-8 ድረስ ሆነው በመሆን እንስሳን ያድናሉ። ጫካዎች ውስጥ የሚኖሩ ሆነው በአንደኝነት ደግሞ ከስዊድን ጋር በሚያጎራብቱ ቦታዎች ይኖራሉ።


©Kjell-Erik Moseid/Samfoto©Kjell-Erik Moseid/Samfoto

እባብ (እፉኝት)

እፉኝት ኖርዌይ ውስጥ የሚገኝ መርዛም የሆነ የእባብ አይነት ነው። እፉኝት በቀላሉ ተለይቶ ይታወቃል ምክኒያቱም ወገቡ ላይ ተጣጣፊ የሆነ ቀለም አለው። አይጦችን እና ሌሎች ትንንሽ እንስሳት ይመገባል። የሚናከሰው አደጋ ላይ እንደሆነ ሲያውቅ ብቻ ነው። በእፉኝነት ከተነከሳችሁ ከተቻለ ያጋጠማችሁን ነገር እንደ ቀላል ወሰዳችሁ የሕክምና እርዳታ ልትጠይቁ ይገባል።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no