Intro
Amharisk • አማርኛ

የሳሚ (Sámi)

©Trym Ivar Bergsmo/Samfoto©Trym Ivar Bergsmo/Samfoto

የሳሚ ሕዝብ በሰሜናዊ የኖርዌይ ስዊድን ፊንላድ እና ሩስያ ክፍሎች ለረዥም ዘመናት በመሮር ላይ ያሉ የመጀመሪያ ሰፋሪ ሕዝብ(ተወላጅ) ናቸው። የመጀመሪያ ሰፋሪ (ተወላጅ) ሲባል በአንድ አገር ውስጥ ለረዥም ጊዜ በመኖር ላይ ያለ ሕዝብ ማለት ነው።

የሳሚ ሕዝብ ብዛት ወደ 100000 አካባቢ የሚገመት ሲሆን ከ40ሺህ እስከ 50ሺህ የሚሆነው የሕዝብ ብዛት ኖርዌይ ውስት ይኖራል።

የሳሚ ሕዝብ ቋንቋ ሳሚ ተብሎ የሚጠራ የራሱ ቋንቋ አለው። የሳሚ ቋንቋ የተለያዩ ቀበለኛ ንግግር(ዘዬ) ስላለው ሁሉም የሳሚ ሕዝብ ደግሞ የነብስ ወከፍ ቀበለኛ(ዘዬ) የሚረዳው አይደለም። በአሁኑ ሰአት በብዙ ሺህ የሚሆነው የሳሚ ሕዝብ ክርስቲያን ቢሆንም የሳሚ ሕዝብ ግን የራሱ የሆነ ባህልና እና ሓይማኖት አለው። የሳሚ ሕዝብ የራሱ የሆነ ሙዚቃ ስልት አለው። አብዛኛው ሰው የሳሚ ሕዝብን ሙዚቃ ከዩይክ ጋር ያመሳስለዋል። ዩይክ ማለት እየዘፈንክ ድምጽህን እንደ ሙዚቃ መሳሪያ እየተጠምክ የምትጫወተው ነው።

ቀደምት የሆነው የሳሚ ሕዝብ በአደን እና ዓሣ በማጥመድ ኑሮውን ይገፉ ነበር። አንድ አንድ የሳሚ ሕዝቦች በሰሜናዊ ኖርዌይ ሰፊ ቦታዎች ሰፍረው ብዛት ያላቸው አጋዘኖችን እና እንስሳትን ያረቡ ነበር። በአሁኑ ወቅት የሳሚ ሕዝብ 10 በመቶ አካባቢ የሚሆነው ብቻ እረይ እና አጋዘን በማርባት ይኖራሉ። አብዛኞቹ ደግሞ ሌላ አይነት ሥራ ይሰራሉ።

አብዛኛው የሳሚ ሕዝብ ከዚች አገር አስተዳደር ከተማዎች መካከል አንዷ በሆነችው ኦስሎ ውስጥ የሚኖር ሲሆን በብዙ የሚቆጠር የሳሚ ሕዝብ ግን እስከ አሁን ድረስ በስሜናዊ ኖርዌይ ውስጥ ይኖራል።

የመጀመሪያው የሳሚ ቲንግ (ፍ/ቤት) በ1989 ኖርዌይ ውስጥ ተከፍቷል። የሳሚ ቲንግ በዲሞክራሲያዊ አገባብ በሳሚ ሕዝብ የተመረጠ ሸንጎ ነው። የሳሚ ቲንግ እንደ ባሕል ትምህርት በተሣሰሉት ሌሎተ ዘርፎች እና የሳሚ ሕዝብ ጉዳዮች ዙሪያ ይሰራል።

የሳሚ ህዝብ ተወላጅ ወይም ጥንታዊ ህዝብ ነው። ከዚህ አንፃር በመላው ዓለም ስለሚገኙ ተወላጅ ወይም ጥንታዊ ህዝቦች ተወያዩ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no