Intro
Amharisk • አማርኛ

ርዕስ 7 የሕዝብ ቅርጽ እና አይነት

ከ18,000 ዓመታት በፊት ኖርዌይ በበረዶ የተሸፈነች አገር ነበረች። ቀስ በቀስ እየሞቀች ስለመጣች በረዶው ቀለጠ። ወደዚህ አገር የመጡ የመጀመሪያ ሰዎች በረዶው መቅለጥ ከጀመረ ከ11ሺህ ዓመታት በኋላ ከጀርመን ወደዚህ የመጡ ሰዎች ናቸው። ኑሮአቸውን እንሰሳት በማደን ይመሩ ነበር። ለመሣሪያም ድንጋይ ይጠቀሙ ነበር። ልብሶቻቸውም ከእንስሳት ቆዳ የተሰራ ነበር። ይህንን ዘመን የድንጋይ ዘመን በማለት እንጠራዋለን።

ከጊዜ በኋላ አካባቢው እየሞቀ ስለመጣ ትልልቅ ጫካዎች መፈጠር ጀመሩ። ሕዝቡ ደግሞ መሬት ማረስ እና እንስሳት ማርባት ጀመረ። ፈትል መፍተል እና ልብስ መሥራት(ሽመና) ጀምረው እና ከበግ ፀጉር ልብስ መሥራት ችለው ነበር። ቢላዋዎች ፋስ እና ሌሎች መሣሪያዎችን ከብረት ይሰሩ ነበር። የቅርብ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ይኖሩ ነበር። ወንድ አያት የቤተሰቡ እርሻ ኃላፊ ነበር። ሁሉም የቤተሰብ አባል ከቤተሰቡ ዋስትና ጥበቃ እና እገዛ ይሰጠውም ነበር። በትልልቅ ቤተሰቦች መካከል ለምያጋጥም ግጭት በፍርድ ይፈታ ነበር። አንዳንዶቹ ትልልቅ ቤተሰቦች ሐብታሞች እና ሐይለኞች ስለነበሩ ከሌሎች የአውሮፓ ሕዝቦች ጋር የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር።

በ793 ኖርዌጂያዊያን በሰሜናዊ እንግሊዝ ምስራቃዊ የባሕር ዳርቻ የምትገኝ ደሴት ሊንድስፋርነ (Lindisfarne) የነበረች ገዳምን አጠቁ። ከኖርዲክ ዞን ለሆኑ ሕዝቦች በአውሮፓ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ሲውዲናዊያን ዴንማርካዊያን እና ኖርዌጂያዊያን የተሻሉ መርከቦች ስለነበራቸው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ማድረግ ጀመሩ። ቫይኪንግስ (Vikings) ተብለው ይጠሩ ነበር። ይነግዱ፣ ይዘምቱ፣ ይዋጉ፣ እና ባሮችን ይወስዱ ነበር። ቫይኪንግስ ኖርዌይን በመተው በሌሎች ቦታዎች ለመስፈር ይሄዱ ነበር።

©O. Væring Eftf. AS©O. Væring Eftf. AS

ይህ ድሕረ ገጽ በመማሪያ መፀሐፍ ውስጥ የሚገኘው 7ኛ ርዕስ ተጨማሪ ነው። ስለሚከተሉት ርዕስቶች በተመለከተ እዚህ ላይ በተጨማሪ ማንበብ ትችላላችሁ ፤

  • ኖርዌይ በድምጽ እና በስእል
  • መጓጓዣ
  • የሳሚ (Sámi) ሕዝብ
  • ነዳጅ
  • ወደ ገጠር አካባቢዎች (Allemannsretten) የመጓዝ መብት
  • የእረፍት ጊዜ ዓሣ ማጥመድ
  • ኖርዌይ ውስጥ የሚገኙ የታወቁ እንስሳት

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no