Intro
Amharisk • አማርኛ

አስገዳጅ ጋብቻ

በእድሜ ትንሽ የሆነች ወጣት ሴት ወይም ወንድ እንዲያገቡ በቤተሰብ ጫና ሲደረግባቸው አስገዳጅ ጋብቻ ነው ማለት ነው። ይህ ጫና አካላዊ ወይም ስነ አእምሮአዊ ሊሆን ይችላል። ኖርዌይ ውስጥ አንድ ሰው እንዲያገባ ማስገደድ ወይም ጫና ማድረግ ህገወጥ ነው። በኖርዌይ ህግ የአስገዳጅ ጋብቻ እንደ ትልቅ ወንጀል ይቆጠራል። አንድ ወጣት ከህግ ውጪ ከኖርዌይ በማስወጣት ወደ ሌላ ሀገር ወስዶ እዚያ እንዲያገባ/እንድታገባ ማስገደድም ህገወጥ ነው።

ባለፉት ቅርብ አመታት ተሰድደው በመጡ ወጣቶች መካከል የሚደረግ አስገዳጅ ጋብቻ በሰፊው የሚነገርለት ርዕስ ሆኖ ይገኛል። ፖለቲከኞች እና ሌሎችም አስገዳጅ ጋብቻን እንደ ትልቅ ችግር ያዩታል። የሚቆምበት መንገድ ለማግኘትም እየሞከሩ ነው።

የኖርዌይ ህግ ስለ ጋብቻ ምን ይላል?

«ወንዶች እና ሴቶች የትዳር አጋሮቻቸውን(ባል ወይም ሚስት) በነጻነት የመምረጥ አንድ አይነት መብት አላቸው። በፍቃደኝነት እና ስምምነትም ወደ ጋብቻ መግባት አለባቸው።» ከጋብቻ አዋጅ ክፍል § 1a የተወሰደ ነው።

«ባስገዳጅ ሰርግ ጉዳይ ላይ በአመጻ፣ ነጻነት በመግፈፍ፣ ያለአግባብ ተጽእኖ በማድረግ ወይም ሌሎች ህገወጥ የሆኑ ነገሮች በመፈጸም ወይም እንደዚህ አይነት ተግባር ለመፈጸም ወደ ጋብቻ ለመግባት ያስገደደ ማንኛውም ሰው ይቀጣል። የአስገዳጅ ጋብቻ ቅጣትም 6 አመት ነው። መርዳት እና መተባበርም ልክ እንደዚሁ ያስቀጣል።» ከኖርዌይ ወንጀለኛ ህግ ክፍል 222 ንኡስ ክፍል የተወሰደ ነው።

ለማግባት ጫና ተደርጐብናል በለው የሚያምኑ ወጣቶችን ለመርዳት የሚሞክሩ ብዙ ማህበራት አሉ።

ለምሳሌ የኦስሎ የአህጉራዊ ቀይ መስቀል ማእከል (ORKIS) የአስገዳጅ ጋብቻ መጠቆሚያ የአስቸኳይ ጊዜ የስልክ መስመር አለው። እርዳታ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ወይንም ሌላ ሰው ማነጋገር የምትፈልጉ ከሆነ ልትደውሉላቸው ትችላላችሁ። እዚህ ማህበር ውስጥ የሚሰራ ሰው ሚስጢር የመጠበቅ መብት አለበት። ስማችሁን ለመስጠት አትገደዱም። ስልኩ በነጻ ነው፡፡ በስራ ቀናት ከ3፡00 ጠዋት እስከ 12፡00 ከሰዓት በኃላ ድረስ መደወል ትችላላችሁ። ስልክ ቁጥሩም 815 55 201 ነው።

ኃይልን (ማስገደድን) እንዴት ትገልጹታላችሁ?

የኖርዌይ ህብረተሰብ ለምንድን ነው አስገዳጅ ጋብቻን እንደ ችግር የሚያየው?

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no