Intro
Amharisk • አማርኛ

የቤት ንብረት መድህን

የቤት ንብረት መድህን ግዴታ አይደለም። ነገር ግን መድህን ቢኖር ጠቃሚ ነው። የግል ቤትም ሆነ የኪራይ ቤት የምንኖር ከሆነ የቤት ንብረት መድህን ሊኖረን ይገባል።

የቤት ንብረት መድህን የቤት እቃ፣ የቢሮ፣ ቴሌቭዥን፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች እና ልብሶች እና ሌሎች ነገሮች ላይ የእሳት ወይም የውሃ አደጋ ቢያጋጥም በአጋጠመው አደጋ ምክንያት የወጣው ወጪ የሚሸፍን ነው። ይህ መድህን ቤት ውስጥ ያጋጠመው ስርቆትንም ይሸፍናል።

በእንደዚህ አይነት መድህን መግባት የራሳችን ኃላፊነት ነው። የቤት ንብረት መድህን ሞላውን ንብረታችን እና ቤታችንን የሚመለከት ነው። የቤት ንብረት መድህን በምንገባበት ወቅት ከፍተኛው የመድህን ድምር ስንት መሆን እንዳለበት የምንደምር እራሳችን ነን። ከፍተኛ የመድህን መጠን ከመረጥን የመድህን ክፍያውም ይጨምራል። እድለኛ ካልሆኑ ዝቅተኛው የመድህን መጠን ከመረጡ ሊወደድብዎ ይችላል።

የቤት መድህን ከመግባታችሁ በፊት ውሎች እና ስምምነቶች እንደዚሁም የተለያዩ መድህን ድርጅቶች የመድህን ዋጋቸውን ማየት ያኖርባችኋል።

አብዛኛዎች የመድህን ድርጅቶች ባላቸው ድረገጾች ብዙ መረጃ ይሰጣሉ። ለምሳሌ የቤት የመድህን ንብረት ዋጋዎች ምን ያህል እንደሆኑ ማየት ይችላሉ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no