Intro
Amharisk • አማርኛ

የራስ የሆነ ቤት ባለቤት መሆን

ከኖርዌይ ህዝብ 74 በመቶ የራሳቸው ቤት አላቸው።

የቤት ባለቤት የምትሆንባቸው የተለያዩ መንገዶች አሉ። በጣም የታወቁት መንገዶች

  • የግል ቤት
  • የድርጅት ቤት

የቤት ባለንብረት

የቤት ባለቤት ከምንሆንባቸው መንገዶች አንዱ ለመኖሪያ ቤት የግል ቤት ሲኖረን ነው። በግል ቤት በመግዛት ስንፈልግ የራሳችን ገንዘብ መሰብሰብ ይኖርብናል። ከባንክ መበደር የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን ንብረት ያስፈልጋል።

የግል የሆኑ የተለያዩ የቤት አይነቶች አሉ። በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ሁለቱም

  • የግል የብቻ የሆነ ቤት አፓርታማ ያልሆነ
  • የጋራ መኖሪያ ቤት ለምሳሌ አፓርታማ ወየም የተደረደሩ ቤቶች

የግላችን በሆነ ቤት የምንኖር ከሆነ የቤቱ ሁሉም ኃላፊነቶች ለምሳሌ የፈይናንስ እና የማስተካከል የኛ ይሆናል። የአገልግሎት ክፍያዎች ለምሳሌ የአካባቢ ባለስልጣን የህንጻ መድህን ክፍያዎች (ውሃ፣ የቆሻሻ ማጠራቀም እና ማንሳት) በቀጥታ የቤቱ ባለቤትን ይመለከታል።

ባለቤት በሚኖርበት የጋራ መኖሪያ አካባቢ እየኖርን ከሆነ የምንኖርባቸው ክፍሎች እና አፓርታማ የራሳችን መሆን አለበት። ቤቱ ያረፈበት መሬት ግን ከሌሎች ክፍሎች ባለቤቶች ጋር የጋራ መሆን አለበት። የአገልግሎት ክፍያዎች ለምሳሌ የአካባቢ ባለስልጣን የህንጻ መድህን ክፍያዎች በቀጥታ ወደ ተከራዮች ኮሚቴ ማህበር ገቢ ይደረጋል። ወጪዎቹም በነዋሪዎች መካከል ይከፋፈላል። እነዚህ ወጪዎች የጋራ የአገልግሎት ክፍያዎች ተብለው ይጠራሉ። እንደተለመደው የአገልግሎት ክፍያዎች በክፍሎቹ ስፋት መሰረት ነው የሚከፋፈሉት። ይህ ማለት በአነስተኛ ክፍል የሚኖር ነዋሪ ሰፊ ክፍል ካለው ጋር ሲነጻጸር አነስተኛ የሆነ ወርሀዊ የአገልግሎት ክፍያ ይከፍላሉ። በተከራዮች ማህበር በአብዛኛው ጊዜ የጋራ እዳ የሚባል ነገር የለም።

የድርጅት ቤቶች

የድርጅት የሆኑ ቤቶች ህንጻው (የአፓርታማ ክፍሎች፣ በተርታ የተደረደሩ ቤቶች፣ ለብቻ የተለዩ የሚመስሉ ቤቶች፣ ለብቻቸው የተለዩ ቤቶች) በድርጅት ባለቤትነት የተያዙ ናቸው። የድርጅት ከሆኑ ቤቶች ብንገዛ፣ የድርጅት ከሆኑ ቤቶች ውስጥ አንድ የተወሰነ ክፍል ውስጥ ሊያኖረን የሚችል መብት እየገዛን ነው ማለት ነው።

የድርጅት ቤቶች ሁለት አይነት ናቸው።

  • ከሚሰሩት የእርዳታ ቤቶች ጋር ትስስር ያላቸው የድርጅት ቤቶች
  • የማንኛውም ድርጅት ቤቶች

የድርጅት የሆኑ ቤቶችን ስንገዛ በእርዳታው ከተያዙት ቤቶች የኛን ድርሻ እየገዛን ነው ማለት ነው (መኖርያ ዋጋውንም እንከፍላለን።) የዚህ ድርሻን ዋጋ ለመክፈል ገንዘብ ሊኖረን ይገባል። ለዚህ ቤት ድርሻ የሚከፈለው ገንዘብ የቤቱን ትክክለኛ ዋጋ ከፊሉ እንደሆነ መሆኑን መረዳት ያስፈልገናል። ትክክለኛ ዋጋውን ለማወቅ የድርጅት የሆኑ ቤቶች እዳ እንዲሁም ከግምት ውስጥ መግባት አለበት።

አብዛኛውን ጊዜ የድርጅት ቤቶች የአፓርታማ ክፍሎች የአገልግሎት ክፍያ የተከራዮች ማህበር ከተሰበሰበ ባለቤቶች ከሚኖርበት ቤቶች የበለጠ ነው። ይህም የአገልግሎት ክፍያዎች የእርዳታ ቤቶች ከዝቅተኛ እዳ ጋር የእርዳታ ድርጅት ቤቶች፣ የአካባቢ ባለስልጣናት ክፍያዎች፣ የህንጻ መድህን፣ የኤሌትሪክ ክፍያ፣ የጋራ ቦታ እና ሌሎች ከእንክብካቤ ጋር የተያያዙ ወጪዎች፣ ወለድና የብድር ክፍያዎች የሚሸፈን ስለሆነ ነው።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no