Intro
Amharisk • አማርኛ

የስራ ማመልከቻ

አሰሪዎች ያላቸውን ክፍት የስራ ቦታ ለመሙላት ብዙ ቁጥር ያላቸው የስራ ማመልከቻዎችን ይቀበላሉ። ብዙ ጊዜም ለቃለመጠይቅ እንድትጠሩ እና እንዳትጠሩ የሚወስነው ያቀረባችሁት የስራ ማመልከቻ ነው። ለምታቀርቡት ማመልከቻ ስለራሳችሁ እና ስላለፈው ታሪካችሁ እንደዚሁም ላለው ክፍት የስራ ቦታ በምን መልኩ ብቁ እንደሆናችሁ በአጭሩ ግለጹ። ያላችሁም ለየት ያለ ችሎታ ምን እንደሆነ ማሳወቅ አስፈላጊ ነው። ባለው ክፍት የስራ ቦታ እንዴት ያለ መስፈርት እና ብቃት ልታሳዩ ተችላላችሁ? የስራ ማመልከቻ ስትጽፉ ስለራሳችሁ በኩራት መናገር ተቀባይነት ቢኖረውም ሀቀኛ መሆን ግን አስፈላጊ ነው።

የምታቀርቡት ማመልከቻ ሲታይ ደስ የሚያሳይ ንጹህ መሆን ይገባዋል። ኮምፒውተር በመጠቀም ወይም ታይፕ በመጠቀም ቢጻፍ ይመረጣል። የማመልከቻው ይዘት ትክክል መሆን አለበት። ይህም አድራሻዎችን ወይም ስልክ ቁጥሮችን እንደዚሁም ስለራሳችሁ እና ስራ ልምዳችሁ የምታቀርቡትን መረጃ ይመለከታል። ብዙ የቃላት ስህተት ወይም የፊደል ግድፈት በስራ ማመልከቻው መፈጸም ጥሩ አይደለም። የስራ ማመልከቻ አጻጻፍን በተመለከተ አንድ አይነት አገበብ አለ። በላይኛው ግራ በኩል ስማችሁ እና አድራሻችሁ በመጻፍ ትጀምራላችሁ። ከስሩ እያመለከታችሁበት ያላችሁትን የአሰሪ ስም እና አድራሻ ትጽፋላችሁ። ቀን እና ቦታን በቀኝ በኩል በአሰሪ አድራሻችሁ መጨረሻ መስመር ላይ መጻፍ ይገባችኋል።

ማመልከቻው የሚከተሉት ነጥቦችን መያዝ አለበት።

  • እያመለከታችሁበት ያለው የስራ ቦታ
  • ስለ ክፍት የስራ ቦታ እንዴት እንደሰማችሁ
  • ስለ እራሳችሁ እና በአሁን ምን እያደረጋችሁ እንደሆነ የሚገልጽ አጭር መግለጫ
  • ስላላችሁ ያለፈ ታሪክ የሚያሳይ አጭር መግለጫ
  • ለስራው ብቁ የመሆናችሁ ምክንያት

በማመልከቻው ላይ ሙሉ ስማችሁ ያለበት ፊርማ እንደሚስፈልጋችሁ አስታውሱ።

ከማመልከቻው ጋር የሚከተሉትን አያይዛችሁ መላክ ጥሩ ነው።

  • አጭር የሕይወት መረጃ ታሪክ (CV)
  • የምስክር ወረቀቶች ቅጂ
  • ባለፉት ስራዎች የተሰጡ የምስክር ደብዳቤዎች ቅጂ

አጭር የሕይወት መረጃ ታሪክ (CV) ያላችሁ ትምህርት፣ የስራ ልምድ ወዘተ በየነጥቡ የምትዘረዝሩበት ሰነድ ነው።

በቀኝ በኩል የሚገኘውን የስራ ማመልከቻ ምሳሌ ተመልከት።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no