Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV)

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) ዋነኛ ስራ በተቻለ መጠን ስራ ፈላጊዎች በፍጥነት ስራ እንዲያገኙ መርዳት ነው። የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) ፈጣን የሆነ የስራ አፈላለግ ሁኔታ እንዲኖር ይረዳል። የግል ክትትል እና አስተዳደርን ይሰጣል። የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) ስራ ፈላጊዎች ብቃት እንዲኖራቸው ይሰራል።

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV)፣ ኖርዌይ ውስጥ ስለሚገኘው የስራ ገበያ ሰፊ እውቀት አለው። የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) ስራ አጥነት ሁኔታን ለመከላከል ከአሰሪዎች፣ ባለስልጣኖች እና ድርጅቶች ጋር በቅርበት ይሰራል።

መረጃ

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) አስተዳደር ዋነኛ አላማ አገናኝ በመሆን በመስራት ስራ ፈላጊዎች ስራ እንዲያገኙ መርዳት ነው። ይህም ለስራ ፈላጊዎች በሚመለከታቸው የስራ አይነት መረጃ መስጠት ነው። ማስታወቂያዎች እና ክፍት የስራ ቦታዎችን በተመለከተ የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) አስተዳደር ድረገጽን መመልከት ትችላላችሁ።

ልምድ ማካበት

ስራ እንዲያገኙ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ስራ ፈላጊዎች በተለያዩ ኮርሶች አማካኝነት ሌላ የተዘጋጁ ስልጠናዎች እና ስራ ስልጠናዎች እና ልምድ ያካብቱ ይችላሉ።

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro)

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro) ተሰድደው የመጡትን ስራ ፈላጊዎች ድጋፍ የመስጠት የተለየ ኃላፊነት ያለው የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) አስተዳደር የሚገኝ የተለየ ክፍል ነው። የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro) በኦስሎ፣ በርገን፣ ክሪስቲያአንሳንድ እንደዚሁም ትሮንድሀይም የሚገኙ ጽ/ቤቶች አሉት። ከሌሎች ሀገሮች የወጡ አመልካቾች በኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro) ለሚገኝ ድጋፍ ማመልከት ይችላሉ። የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro) አስተዳደር ዋነኛው ስራ በስደት ለመጡት ስራ ፈላጊዎች የሚሆኑ አገልግሎቶች እንዲሰጥ ለእያንዳንዱ የአካባቢ ባለስልጣን ከኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት (NAV) አስተዳደር ጋር በመሆን በአንድነት መስራት ነው።

የኖርዌይ ስራና ሰብአዊ ደህንነት ኢንትሮ (NAV Intro) አስተዳደር በሚከተሉት ጉዳዮች ድጋፍ ሊሰጥ ይችላል።

  • የቃለመጠይቅ ምክር መመሪያ
  • የቋንቋ ፈተና
  • የመዘጋጃ ስልጠና
  • በስደት ከመጡት ስራ ፈላጊዎች ጋር የሚሄዱ የተለያዩ ኮርሶች

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no