Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌይ ትምህርት አጭር ታሪክ

©J.W. Cappelens arkiv©J.W. Cappelens arkiv

እስከ 1700 አጋማሽ አብዛኛዎቹ ኖርዌጂያዊያን ያልተማሩ ነበሩ። ጥቂቶቹ ብቻ ማንበብ እና መጻፍ ይችሉ ነበር።

በእዚህ ጊዜ ቤተክርስቲያን ሰው መጽሐፍ ቅዱስ አንብቦ እንዲችል አስፈላጊ ነው የሚል እምነት ነበራት። ስለዚህም ኖርዌይ የመጀመሪያ የትምህርት አዋጅ በ1739 አወጀች። ልጆች ማንበብ እና ስለ ክርስትና ትምህርት ቤት ውስጥ ይማሩ ነበረ። በ1827 የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፣ ሂሳብ እና መዝሙር እንደ የትምህርት ክፍሎች መሰጠት ጀመሩ። ልጆች በየአመቱ ለጥቂት ሳምንታት ወደ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ ይፈቀድላቸው ነበር። ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ልጆች በገጠር ውስጥ ከሚኖሩት ልጆች የበለጠ ወደ ትምህርት ቤት ይሄዱ ነበረ። ልጆች እድሜያቸው 7 ከደረሰ በኋላ ትምህርት ይጀምሩ ነበረ። እድሜአቸው 14 ሲደርስም ይጨርሱ ነበር። (በቤተክርስቲያንም ማረጋገጫ ይሰጣቸው ነበር።)

በ1936 የ7 አመት አስገዳጅ ትምህርት ተጀመረ። ነገር ግን የሚሰጠው ትምህርት ለሁሉም ሰው አንድ አይነት አልነበረም። ለምሳሌ ወንዶች ከሴቶች በላይ ሂሳብ ይማሩ ነበር። ሴቶችም ስለ ቤት አያያዝ እና ምግብ አሰራር ይማሩ ነበር።

ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኋላ (1939-1945) ግን የእኩልነት ሀሳቦች እና እኩል ክብር በኖርዌይ ህብረተሰብ አስፈላጊ ሆነ። በትምህርት ላይም ሊሰራ የሚችል ሆነ። ሁሉም ተማሪዎች እኩል ክብር ያለው ትምህርት እንደሚሰጣቸው ተደረገ። በሀብታም ልጆች እና ድሃ ልጆችም መካከል ምንም አይነት ልዩነት እንዳይኖር ተደረገ። ሴቶች እና ወንዶች አንድ አይነት ትምህርት እንዲሰጣቸው ተደረገ። እንደዚሁም በዚህች ሀገር ማንኛውም ቦታ ላይ ቢሆንም ምንም ልዩነት እንዳይኖር ተደረገ።

በ1969 አስገዳጅ ተምህርቱ ለ9 አመት ሲራዘም በ1997 ለሁሉም ሰው የሚመለከት እስከ 10 አመት እንዲራዘም ተደረገ።

©Olav Olsen/Scanpix©Olav Olsen/Scanpix

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no