Intro
Amharisk • አማርኛ

የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት (State Educational Loan Fund)

የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት ለተማሪዎች ገንዘብ የሚያበድር እና ድጋፍ የሚሰጥ የመንግስት ባንክ ነው። ምንም እንኳን የዞን ጽ/ቤቶች በስታቫንገር፣ በርገን፣ ኦርስት፣ ትሮንድሃይም፣ እንደዚሁም ትሮምሶ ቢኖሩም የመንግስት ብድር ተቋም ማዕከላዊ ጽ/ቤት ግን ኦስሎ ውስጥ ይገኛል።

የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት አላማ ማንኛውም በከፍተኛ ትምህርት መማር የሚፈልግ ሰው መማር እንዲችል መርዳት ነው። ከፍተኛ ትምህርት ለመማር ያለው እድል በምትኖርበት ሀገር ጆግራፋዊ አቀማመጥ፣ እድሜ፣ ጾታ እንደዚሁም የገንዘባዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች ተጽእኖ የማይደርስበት ነጻ መሆን ይኖርበታል። የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት በ1974 ተቋቋመ።

ምንም እንኳን ኖርዌይ ውስጥ የሚሰጥ ከፍተኛ ትምህርት ነጻ ቢሆንም ተማሪዎች ለመኖሪያ የሚሆናቸው ገንዘብ ሊኖራቸው ይገባል። ለመጻሀፍ እና ለሌሎች የትምህርት እቃዎች፣ ለመኖርያ ቤት፣ ምግብ እና ልብስ ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል። ብዙ ተማሪዎች እየተማሩ በትርፍ ጊዜአቸው እየሰሩ ቢሆንም አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ከመንግስታዊ ብድር ተቋም ለትምህርት ገንዘብ ይበደራሉ።

ተማሪ ፈተና ካለፈም የብድሩ የተወሰነ ክፍል ወደ እርዳታ ይቀየርለታል። የሚሰጡት ድጋፎችም የማይመለሱ ናቸው።

የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት በአሁኑ ወቅት 740,000 ደንበኞች አሉት። ከ2003-2004 ባለው ጊዜ 263,000 የሚሆኑ ደንበኞች የትምህርት ድጋፍ ተሰጥቷቸዋል። እነዚህም በአጠቃላይ 9.7 ቢሊየን የኖርዌይ ከሮነር ተበድረዋል። እነዚህ ደንበኞች በአሁኑ ወቅት 6.7 ቢሊየን የኖርዌይ ክሮነር በእርዳታ መልክ ተቀብለዋል።

የተማሪዎች ብድርን በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጋችሁ የመንግስት ብድር ተቋም ለትምህርት (State Educational Loan Fund) ድረገጽ መመልከት ትችላላችሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no