Intro
Amharisk • አማርኛ

የውጪ አገር ትምህርት እና የሙያ ስልጠናዎች ማረጋገጫዎች መጽደቅ

ወደ ኖርዌይ የሚመጡ ብዙ ስደተኞች በሌላ ሀገር የትምህርት መስፈርቶች ወይም የስራ ልምድ ያላቸው ናቸው። ከኖርዌይ ውጪ በሌሎች ሀገሮች ትምህርታዊ መስፈርቶች ያገኙ ከሆነ ያሉዎት ትምህርታዊ መስፈርቶች እዚህ ተቀባይነት እንዳለው ማረጋገጥ ይገባቸዋል። ምናልባት ካላችሁ የትምህርት መስፈርቶች የተወሰነውን ክፍል ብቻ ተቀባይነት ሊያገኝ ይችላል። ይህም ተጨማሪ ኮርሶች መውሰድ ሊያስፈልጋችሁ ይችላል ማለት ነው።

አብዛኛዎቹ ጊዜአት ሄደቱ ረዥም ጊዜ ስለሚወስድ ያላችሁን ትምርታዊ መስፈርቶች ተቀባይነት እንዲያገኝ በተቻለ መጠን ፈጥናችሁ ስራውን መጀመር ያስፈላጊ ነው። ብዙ ተቋሞዎች የተለያዩ የትምህርታዊ መስፍቶች አይነት ለጽደቅ ወይም ለማረጋገጥ ኃላፊነት ይወስዳሉ። የኖርዌይ የትምህርት ብቃት ማረጋገጫ ተቋም (NOKUT) ያላችሁን የምስክር ወረቀት ወደ ሚመለከተው አካል ሊልከው ይችላል። ያላችሁን የትምህርት መስፈሮች በሙሉ ወይም በከፊል ተቀባይነት ሊያገኝ ይችላል። አስፈላጊ ከሆነም ትምህርታችሁን ኖርዌይ ውስጥ ልትቀጥሉ ትችላላችሁ።

የውጪ አገር ትምህርታዊ መስፍርቶችን ለማረጋገጥ በኖርዌጂያን የትምህርት ብዛት ማረጋገጫ ተቋም (NOKUT) ድረገጽ በበለጠ ማንበብ ትችላላችሁ።

የስራ ልምድ ካላችሁ ለሙያ ፈተና መመልከት ትችላላችሁ። የሙያ ፈተና አዋቂዎች ከአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሙያ አይነቶች ወይም የእውቀት ዘርፎች ያላቸውን ችሎታ እና እውቀት ለማስመሰከር ይረዳቸዋል። ያላችሁን የድሮ ታሪክ፣ ትምህርታዊ መስፈርቶች፣ የስራ ልምድ፣ የቋንቋ ችሎታ እና የግል ግቦች ይመረመራል። የሙያ ፈተና መውሰድ የሚፈልጉ ሰዎች ባላቸው የፈተና ዘርፍ በትምህርት እና በተግባር ፈተና መውሰድ ይገባቸዋል። ከፈተና በኋላ የእጅ ስራዎች ምስክር ወረቀት ማግኘት እንድትችሉ ባላችሁበት የእውቀት ደረጃ ያለውን ሁሉንም ዘርፎች የሚመለከት ስልጠና ሊሰጣቸው ይገባል። መልካም እውቀት ያላችሁን ዘርፎች አይነት የሚገልጽ የጽሁፍ ሰነድ መቀበልም ትችላላችሁ።

የሚደረገውን መደበኛ ያልሆነው የትምህርት መስፈርት ግምገማ እና የሙያ ፈተናዎች እና ማን ይከፍላል በሚለው ጉዳይ ላይ የተለያዩ መመሪያዎች ይጠቀማሉ። ለበለጠ መረጃ በአካባቢዎ የሚገኝ ባለስልጣን የስራ አገልግሎት ጽ/ቤት ወይም የሀገራዊ ደህንነት ጽ/ቤትን መጠየቅ ትችላላችሁ።

ሞያዊ ፈተና ለእናንተ እድል ይከፍትላችኋልን?

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no