Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌጂያን ቋንቋ ስልጠና የተለያዩ ሶስት እርከኖች

ሁሉም ለወጣቶች የሚሰጡ የኖርዌጂያን ቋንቋ ስርዓተ ትምህርት (ሲለቨስ) ተከትለው የሚሰጡ ናቸው። እነዚህ ስርዓተ ትምህርቶች በስቶርቲንጌ(ፓርላማ) የፀደቁ ናቸው። ስርዓተ ትምህርቱ ሰልጣኞች መማር ያለባቸውን እና ማግኘት ስላለባቸው ዕውቀት ዓላማ ይደነግጋል። የስልጠናው ዋናው ዓላማ ሰልጣኙ ኖርዌጂያን መማር እንዲችል እና ስለ ኖርዌይ ሕብረተሰብ በቂ ግንዛቤ እንዲኖረው ነው።

ሰልጣኞቹ ስልጠናውን ለሶስት እርከኖች ከፋፍለው መውሰድ ይችላሉ፤ ይህም በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እና የቀድሞ ትምህርታቸው መሰረት ይወሰናል። ሰልጣኞቹ በስልጠናው ወቅት ከአንደኛው እርከን ወደ ሌላኛው እርከን መሸጋገር ይችላሉ። ዓላማው ኖርዌጂያን ቋንቋን መናገር እና መፃፍ እና መረዳት እንዲችሉ ነው።

1ኛው እርከን

ይህ እርከን ጥቂት ወይም ምንም ትምህርት ላልነበራቸው ተሳታፊዎች አመቺ ነው። አንድ አንድ ተሳታፊዎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው መናገርም መፃፍም አይችሉም።

2ኛው እርከን

ይህ እርከን መጠነኛ የሆነ ትምህርት ላላቸው ተሳታፊዎች አመቺ ነው።

3ኛው እርከን

ይህ እርከን ከፍተኛ የሆነ ትምህርት ላላቸው ሰዎች አመቺ ሲሆን አብዛኛዎቹ የከፍተኛ ደረጃ መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው።

ይህንን ስልጠና ከጨረሱ በኋላ ለፈተና መቀመጥ ይቻላል። አራት የተለያየ ደረጃ ያላቸው ፈተናዎች አሉ። ኖርዌጂያን ፈተና አንድ፣ ኖርዌጂያን ፈተና ሁለት፣ ኖርዌጂያን ፈተና ሶስት እና ኖርዌኛ ፈተና አራት በመባል ይታወቃሉ።

ሙሉ ስርዓተ ትምህርቱን (ሲለቨስ) በድረገጽ VOX (ቪ.ኦ.ኤክስ) ማግኘት ትችላላችሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no