Intro
Amharisk • አማርኛ

የፍርድ ስርዓት

ኖርዌይ ውስጥ ያለው የፍርድ ስርዓት የፒራሚድ ቅርጽ ተዋረድ ያለው ነው።

የዞን ፍ/ቤቶች

የፒራሚድ ተዋረዱ የታችኛው ደረጃ የዞን ፍ/ቤት ተብሎ ይጠራል።

የይግባኝ ፍ/ቤቶች

ቀጥሎ ያለው ደረጃ የይግባኝ ፍ/ቤት ነው። የይግባኝ ፍ/ቤት የይግባኝ ጥያቄዎች የሚቀርብበት አካል ነው። ይህ ማለት በዞን ፍ/ቤት የተሰው ፍርዶች የሚመለከቱ የይግባኝ ውጤት ምን ሊሆን እንደሚችል የሚወስነው የይግባኝ ፍ/ቤት ነው። ተከሳሽ እና ከሳሽ ባለስልጣን ለአንድ ጉዳይ ወደ ይግባኝ ፍ/ቤት የይግባኝ ጥያቄ ማቅረብ ይችላሉ። ቅጣቱ በጣም ከባድ ወይም አነስተኛ ነው ወይም የወንጀል ጥያቄው እንደሚገባ አላገኘንም ብለው የሚያምኑ ከሆነ ይግባኝ መጠየቅ ይችላሉ።

ጠቅላይ ፍ/ቤት

የፒራሚድ ተዋረዱ ከፍተኛው ደረጃ ጠቅላይ ፍ/ቤት ነው። ጠቅላይ ፍ/ቤት የይግባኝ ፍርድ ቤቶች የይግባኝ አካል ነው። በጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጡ ፍርዶች ይግባኝ ሊጠየቅባቸው አይቻልም። በጠቅላይ ፍ/ቤት የሚሰጡ ፍርዶች የመጨረሻ ናቸው። ይህም በሕግ ተግባር ላይ ይውላል ማለት ነው።

ማን ይዳኛል?

በዞኖች ፍ/ቤቶች እና በይግባኝ ፍ/ቤቶች የወንጀል ደረጃና ቅጣት ምን መሆን እንዳለበት ዳኞቹ ይወስኖሉ። ዳኞች፣ ሙያተኛ ዳኞች፣ ተባባሪ ዳኞች ወይም ተራ ዳኞች ሊሆኑ ይችላሉ።

ሙያተኛ ዳኞች፣ ጠበቃዎች ናቸው። ተባባሪ ዳኞች እና ተራ ዳኞች ለዚህ ጉዳይ ተብለው የሚሾሙ ተራ ሰዎች ናቸው። በከባድ ጉዳዮች ላይ የይግባኝ ፍ/ቤት 10 ሲቪል ሰዎች ያሉት የፈራጅ ቡድን ተከሳሹ ወንጀለኛ መሆኑን እና አለመሆኑን ይወስናል። የወንጀል ጉዳዮች በተከሳሽ ጠበቆች ሊወስኑ ይገባቸዋል የሚል በኖርዌይ የህግ ስርዓት ውስጥ በመኖሩ አስፈላጊ አቋም ነው።

የተከሳሽ ጠበቃ

ተከሳሽ እንዲከራከርለት የተሾመ ጠበቃ እንዲኖረው መብት አለው። ተከሳሽ ወደ ፍ/ቤቱ ቀርቦ ስለ እራሱ/እራሷ መናገር ይገባዋል።

የከሳሽ ጠበቃ

ከሳሽ ጉዳዩ የትኞቹን ህጎች እንደጣሰ ምርኩዝ በማድረግ ክሶችን ያቀርባል። እንደዚሁም ከሳሽ ሊሰጠው የሚገባውን ቅጣት ሃሳብ ያቅርባል።

ቅጣት

የተለያዩ ህጋዊ ቅጣቶች አሉ። ከሚከተሉትም በብዛት የተለመዱት ናቸው፤

የተቋረጠ ክስ

የተቋረጠ ክስ ተከሳሹ በማስጠንቀቂያ ሲታለፍ ማለት ነው። ነገር ግን ጉዳዩ ፓሊስ ዘንድ የሚገኘውን ሀገራዊ የክሶች መዝገብ ላይ (National Register of Convictions) ይመዘገባል።

የገንዘብ ቅጣት

የገንዘብ ቅጣት ፍ/ቤት ውስጥ ሳትከስስ የገንዘብ ቅጣት እንድትከፍል እድል ሲሰጥህ ማለት ነው። የገንዘብ ቅጣት አብዛኛውን ጊዜ ለምሳሌ ቀላል ከሆኑት የትራፊክ ህጎች መጣስ ጋር ተያይዞ የሚሰጡ ቅጣቶች ናቸው። የገንዘብ ቅጣት ወደ መንግስት የሚከፈል የገንዘብ መጠን ነው።

ተቀማጭ የእስር ፍርድ

ተቀማጭ የእስር ፍርድ ማለት በአንዳንድ የእስር ሁኔታዎች በዳይ በተፈረደበት የእስር ፍርድ ሳይቀጣ ሲቀር ነው። ሰውየው በሁለት አመታት ውስጥ ከእንደገና ህጉን ከጣሰው በፊተኛው ፍርድ እና በአዲሱ ፍርድ አንድ ላይ ተደምሮ መቀጣት የግድ ይለዋል።

ድንገተኛ የእስር ፍርድ

ድንገተኛ የእስር ፍርድ የተፈረደበት ሰውዬ የግድ የእስር ፍርድ ማግኘት ይኖርበታል። ኖርዌይ ውስጥ የከበደው የእስር ፍርድ የ21 አመታት እስር ሲሆን ሁን ብሎ በመግደል ወይም ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ ከባድ ወንጀሎች ለፈጸመ ሰው የሚሰጥ ቅጣት ነው። በአብዛኛው ጊዜ የእስር ፍርድ የተወሰነባቸው ሰዎች ከእስር ዘመናቸው 2/3ኛውን ካጠናቀቁ በኃላ ምህረት ተደርጎላቸው ይፈታሉ።

ለጥንቃቄ ተብሎ የሚደረግ እስር

ለጥንቃቄ ተብሎ የሚደረግ እስር ህብረተሰቡን በጠቅላላ ለመጠበቅ ተብሎ የሚደረግ እስር ነው። አንድ ሰው ለጥንቃቄ ተብሎ የሚደረግ እስር የሚፈረድበት ከሆነ የተፈረደበት ሰው « ሁኔታውን ሲፈጽመው አእምሮውን ስቶ እንደነበረ» ወይም የአእምሮ በሽተኛ እንደሆነ ወይም ያላደገ ወይም ለወደፊቱ ወደ የአእምሮ ህመም ሊያደርሱ የሚችሉ ችግሮች እንደነበሩት መታወቅ አለበት። የተፈረደበት ሰውም ሌሎችን አዲስ ወንጀሎች ለመፈጸም የመቻል አደጋ ሊኖር ያስፈልጋል።

ለህብረተሰብ የሚሰጡ አገልግሎቶች

የተሰጠው ፍርድ እስከ አንድ አመት የሚደርስ ተቀማጭ የእስር ፍርድ ከሆነ የእስር ፍርዱ ቀርቶ ህብረተሰቡን እንደያገለግል ሊደረግ ይችላል። የአንድ ወር የእስር ፍርድ በቅዳሜ እና እሁድ ወይም ሰውዬው ባለው ትርፍ ሰዓት ከሚሰራው ሰላሳ ሰዓታት የህብረተሰብ አገልግሎት ጋር ተመጣጣኝ ነው።

የህግ ስርዓትን በተመለከተ በኖርዌይ ፍ/ቤቶች ድረገጽ ወይም በድረገጽ Norge.no የበለጠ ማንበብ ትችላላችሁ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no