Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌይ ሀገራዊ የበአል ቀን

የኖርዌይ ሀገራዊ የበአል ቀን ግንቦት 17 ነው። ይህ ቀን ኖርዌይ የራስዋ ህገ መንግስት ባለቤት የሆነችበት 17 ግንቦት 1814ን ለማስታወስ የሚደረግ ነው። በዚህ ሀገራዊ ቀን ሽክ ያለ ልብስ መልበስ የተለመደ ነው። አብዛኛው ሰው «ቡናድ» የተባለ ልብስ ወይም ሌላ የሀገር ባህል ልብስ ይለብሳል። የልጆች ትርኢታዊ ሰልፍ በጠዋቱ ይካሄዳል። የትምህርት ቤት ልጆች የኖርዌይ ባንዲራን እያውለበለቡ መዝሙሮችን እየዘመሩ ሰልፍ ያደርጋሉ። የምረሻ ባንዶችም ብዙ ቦታዎች ላይ ሰልፍ ይወጣሉ። በቀኑ መጨረሻም በትምህርት ቤቶች፣ መዝናኛ ቦታዎች እንደዚሁም በገጠር እና በከተሞች ንግግሮች እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በተከታታይ ይደረጋሉ። 17 መጋቢት እንደ ልጆች ቀን ይታወቃል።

©Bjørn Sigurdsøn/Scanpix©Bjørn Sigurdsøn/Scanpix

የኖርዌይ ሀገራዊ መዝሙር

ኖርዌይ ውስጥ ሀገራዊ የበአል ቀን የልጆች ቀን በመባል ይጠራል። እናንተ የምታውቁት ሌሎች ሀገራት ሀገራዊ ባህላቸውን በምን አይነት ሁኔታ ያከብራሉ?

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no