Intro
Amharisk • አማርኛ

የጾታ እኩልነት

©Hallgeir Vågenes/Scanpix©Hallgeir Vågenes/Scanpix

የጾታ እኩልነት ምን ማለት ነው?

የጾታ እኩልነት ሴቶች እና ወንዶች አንድ አይነት መብት እና ግዴታ ያላቸው ሆነው ማንኛውም ሰው በህብረተሰብ ውስጥ አንድ አይነት እድል አላቸው ማለት ነው። የጾታ እኩልነት በቤተሰብ እና ህብረተሰብ ስለሚኖረው ፍትህ እና የኃላፊነት ክፍፍል ማለት ነው። ጾታ ያሉንን የግል ብልጫዎች እና እጥረቶች ከማየት የሚከለክለን ሲሆን ወደ አድሎ እና የታጠሩ የግለሰቦች እድሎች ሊያመራ ይችላል።

©Scanpix©Scanpix

የኖርዌይ የጾታ እኩልነት አዋጅ (The Norwegian Gender Equality Act)

በ1978 የታወጀ ሲሆን ሁሉም ሴቶች እና ወንዶች እኩል በሆነ አያያዝ ሊያዙ የታለመ ነው። ይህ አዋጅ ምንም እንኳን ሴቶች ያላቸው ቦታ በተለይ የሚያተኩር ቢሆንም ለሁለቱም ጾታዎች ግን አስፈላጊ ነው።

የኖርዌይ የጾታ እኩልነት አዋጅ ከመታወጁ በፊት ሴቶች ለእኩልነት ብዙ አመት ተታግለዋል። ሴቶች ከወንዶች ጋር እኩል የውርስ መብት እንዲኖራቸው በ1854 አስከብረዋል፤ ያላገቡ የደረሱ ሴቶችም እራሳቸውን የሚችሉ ወጣቶች እንደሆኑ በ1864 ተቀባይነት አግኝተዋል። ያገቡ ሴቶች ግን ይህንን መብት እስከ 1888 ድረስ ማስከበር አልቻሉም ነበር። አሁን ግን በራሳቸው ንብረትን ላይ የሚደረገው ማንኛውም ነገር ላይ በተመለከተ በቁጥጥራቸው ስር ነው።

የሴቶች መብት ማህበር (The Norwegian Association for Women's Rights) ኖርዌይ ውስጥ በ1884 ተቋቋመ። አባላቶቹም ሴቶች እና ወንዶች ነበሩ።

©Universitetsbiblioteket i Bergen©Universitetsbiblioteket i Bergen

በ1800 መጨረሻ አካባቢ ሴቶች የፈለጉትን የትምህርት እና ሙያ ለመምረጥ አዲስ እድሎች እንዲኖራቸው ተደረገ። ሴቶች አስተማሪዎች ሆነው እንዲሰሩ ከ1870 ጀምሮ ተፈቀደላቸው። በወቅቱ ህብረተሰቡ በፍጥነት እየተቀየረ ስለነበረ የአዲስ ስራዎች ተፈላጊነትም ከፍተኛ ነበረ። ብዙ ሴቶች በቴሌግራፍ አገልግሎት ወይም የስልክ ክትትል ላይ መስራት ጀመሩ። እነዚህ ሁለቱም ስራ ቦታዎች በአዲስ ቴክኖሎጂ ላይ መሰረት ያደረጉ ነበሩ። ብዙዎቹ አዳዲስ የሴቶች ሙያዎች ስልጠና የሚያስፈልጋቸው ነበሩ። እነዚህ አዲስ እድሎች መሀከለኛ ኑሮ ለነበራቸው ሴቶች በይበልጥ አስፈላጊ ነበሩ።

ዝቅተኛ የስራ አይነት የነበራቸው ሴቶች ለረዥም ጊዜ ፋብሪካዎች ውስጥ የሰሩ ነበር። በ1800 መጫረሻዎቹ እድሜአቸው ለስራ ከደረሱ ሴቶች አንድ ሶስተኛ አካባቢ ገንዘብ በሚከፈሉበት የስራ አይነቶች ተሰማርተው ይሰሩ ነበረ። አብዛኛዎቹም ወጣቶች እና ያላገቡ ነበሩ።

በኖርዌይ የህግ ጾታ እኩልነት ታሪክ የነበሩ አስፈላጊ አመታት

  • 1910 ሴቶች በአካባቢ ባለስልጣን ምርጫዎች ላይ የመምረጥ መብት አገኙ።
  • 1911 የመጀመሪያ ሴት (አና ሮግስታድ) የስቶርቲንጌ ምከትል አባል ሆነች።
  • 1913 ሴቶች ልክ እንደ ወንዶች በምርጫ የመሳተፍ ሁለንተናዊ መብት እንዳላቸው አረጋገጡ።
  • 1922 የመጀመሪያ ሴት (ካረን ፕላቶ) የስቶርቲንጌ አባል ሆነች።
  • 1945 የመጀመሪያ ሴት (ሽስተን ሃንስቲን) የካቢነ ሚኒስተር ሆነች።
  • 1961 የመጀመሪያ ሴት (ኢንግሪድ ብየርኮስ) ቄስ ሆነች።
  • 1968 የመጀመሪያ ሴት (ሊሊ ቦልቪከን) የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነች።
  • 1974 የመጀመሪያ ሴት (ኢባ ሎደን) የዞን አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊ ኖነች።
  • 1978 የመጀመሪያ ሴት (ኢቫ ኮልስታድ) የሴቶች የጾታ እኩልነት ወኪል ተመራጭ ሆነች።
  • 1981 የመጀመሪያ ሴት (ግሮ ሃርለም ብሩንድትላንድ) ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነች።
ግሮ ሃርለም ብሩንድትላንድ (ከስራ ፓርቲ) በ1981 መንግስት አቋቋመች። ለብዙ አመታትም ጠቅላይ ሚኒስተር ሆና ነበረ። ©Helge Mikalsen/Scanpixግሮ ሃርለም ብሩንድትላንድ (ከስራ ፓርቲ) በ1981 መንግስት አቋቋመች። ለብዙ አመታትም ጠቅላይ ሚኒስተር ሆና ነበረ። ©Helge Mikalsen/Scanpix

ስለ ጾታ እኩልነት በበለጠ ማንበብ ከፈለጉ የእኩልነት እና የጸረ አድሎ ወኪል ጽረገጽ ማየት ትችላላችሁ።

ኖርዌይ እኩልነት የሰፈነበት ህብረተሰብ እንዳላት የሚጠቁም ኖርዌይ ውስጥ የምታዩት ምን አለ?
በ1800 መጨረሻዎች እና ከዛ በኋላ ለጾታ እኩልነት ተብሎ ስለተደረገው ትግል ተወያዩ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no