Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌይ የህግ ስርዓት

ስቶርቲንጌ

ኖርዌይ ውስጥ ህጋዊ ስልጣን የሚተገብረው ስቶርቲንጌ ነው። ይህ ማለት ስቶርቲንጌ መደበኛ ህጎች (አዋጆች፣ መመሪያዎችና ህጎች) ያወጣል ማለት ነው።

ሕጋዊ ከለላ

ኖርዌይ ውስጥ ህጋዊ ከለላ (ጥበቃ) እናገኛለን። ይህ ማለት በህግ መሰረት ከተጠቀሰው ፍርድ ውጪ ማንኛውም ሰው ሊፈረድበት ወይም ሊቀጣ አይችልም ማለት ነው።

©Jarl Fr. Erichsen/Scanpix©Jarl Fr. Erichsen/Scanpix

የወንጀል ቅጣት ትዕዛዝ

አብዛኛዎቹ ህጎች ከእነሱ ጋር የሚተሳሰሩ የወንጀል ቅጣት ትዕዛዞች አሉዋቸው። ይህ ማለት ህጉ ሳይከበር ሲቀር ህጋዊ እርምጃዎች እንዲወስዱ ህጉ ያዛል።

ወንጀለኝነት

ወንጀለኝነት ማለት ከተጠቀሱት የወንጀል ቅጣት ትዕዛዞች መካከል አንዳቸው አልተከበሩም ማለት ነው። አንድ ተግባር ወንጀል ሲሆን የሚችለው ተግባሩ ሊያስቀጣ እንደሚችል ህጉ መግለጽ አለበት።

ህብረተሰቡ በየጊዜው እይተለዋወጠ እየመጣ ስለሆነ የሚያስቀጣው ተግባርም እንደተቀየረ ነው። ለምሳሌ እስከ 1972 ወንዶች እና ሴቶች ሳያገቡ አንድ ላይ መኖር ህገወጥ ነበረ። በ2002 ከ16-79 የእድሜ ክልል ውስጥ ካሉት 17%ቱ ሳያገቡ አንድ ላይ ይኖሩ ነበር።

ባለፉት ቅርብ አመታት የተመዘገበው ወንጀል በአስደናቂ ሁኔታ ጨምሯል። ከ1980 እስከ 2000 የተመረመሩ የወንጀለኞች ጉዳይ ቁጥር ከሁለት እጥፍ በላይ ሆኖአል። በ2001 ከተመረመሩት የወንጀል አይነቶች 67.2 በመቶ የሚሆኑት ቤት ገብቶ መዝረፍ፣ ሌብነት እና ከገንዘብ ጋር የተያያዙ ወንጀሎች ነበሩ። ሀይለኛ ወንጀል 7.5 በመቶ ሲይዝ ከአደንዛዥ እጽ ጋር የተያያዙ ወንጀሎችም 14.2 በመቶ ነበሩ። በወንጀል ምክንያት ተከስሰው ከተቀጡት ሰዎች 40 በመቶ በላይ ከ18-25 እድሜ ያላቸው ወጣቶች ናቸው። በወጣቶች የተፈጸሙ የተለመዱ ወንጀሎች መስረቅ፣ ቤት ገብቶ መዝረፍ እና ንብረት ማውደም ናቸው። ኖርዌይ ውስጥ በጣም የተለመደው የእስር ምክንያት ጠጥቶ ማሽከርከር ነው፤ በሌላ አባባል አልኮላዊ መጠጥ ከጠጡ በኋላ መኪና የሚያሽከረኩ ሰዎችን ማለት ነው።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no