Intro
Amharisk • አማርኛ

ስቶርቲንጌ(ፓርላማ)

©Bård Løken/Samfoto©Bård Løken/Samfoto

ስቶርቲንጌ ማለት የኖርዌይ ፓርላማ በሀገሪቷ ውስጥ ከፍተኛ ስልጣን ያለው አካል ነው። ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች የመጡ 169 ተወካዮችም በስቶርቲንጌ ቦታ አላቸው። እነዚህ ተወካዮች በአራት አመት አንዴ ህዝብን ለማገልገል ይመረጣሉ።

የስቶርቲንጌ(የፓርላማ) አስፈላጊ ስራዎች

  • አዳዲስ ህጎችን ማጽደቅ እና ጊዜ ያለፈባቸውን ህጎችን መቀየር
  • ሀገራዊ በጀት ማጽደቅ
  • የመንግስት ስራ እና የህዝብ አስተዳደርን መከታተል።
  • ስለ ፖለቲካዊ ጉዳዮች እና የህዝብ አስተዳደርን መከታተል፡፡

©Jarl Fr. Erichsen/Scanpix©Jarl Fr. Erichsen/Scanpix

በስቶርቲንጌ ውስጥ የሚደረጉ ክርክሮች ለህዝብ ክፍት ናቸው። በክርክር ወቅት መመልከት የፈለገ ማንም ሰው መሳተፍ ይችላል። በክርክር ወቅት ግን የፓርላማ አባላት ብቻ ነው መናገር የሚችሉት። ክርክሩ በስቶርቲንጌ ፕሬዝዳንት ይመራል። አባላቱ በሚወክሉት ክፍል ሀገር መሰረት በመሰብሰቢያ አዳራሽ ይቀመጣሉ።

ለስቶርቲንጌ አባላት በኤሌትሮኒካዊ መልዕክት (ኢ-ሜል) ጥያቄዎች ልትጠቁዋቸው ትችላላችሁ። የሁሉም አባላት ኢ-ሜል አድራሻዎችና ስለ ስቶርቲንጌ በተመለከተ የበለጠ መረጃ በስቶርቲንጌ ድረገጽ ማግኘት ይችላሉ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no