Intro
Amharisk • አማርኛ

የኖርዌይ ታሪክ ፥ ሁለተኛ የአለም ጦርነት

ኖርዌይ ከ1940 እስከ 1945 ድረስ በጀርመን ተወርራ ነበር። በውጊያው ዘመን ብዙ ነገሮች ወድመዋል። ህንጻዎች፣ ፋብሪካዎች፣ መላው ሀገር እና ከተማዎች በቦንብ ጋይተዋል። የብዙ እቃ አቅርቦት እጥረትም ነበር። ብዙ ሰዎችም ከባድ የሆነውን ጊዜ አሳልፈዋል።

ፓላንድ በጀርመን ወታደሮች ከተወረረች በኋላ፣ ሁለተኛ የአለም ጦርነት መስከረም 1939 ተቀጣጠለ። የጀርመን ወታደሮች ሚያዝያ 9 ቀን 1940 ኖርዌይን ወረሩዋት። በዚህች ሀገር ብዙ ቦታዎች ላይ ጥቂት አጫጭር ውጊያዎች እየተካሄዱ ነበረ፤ ጀርመናዊያን ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ኖርዌይን ተቆጣጠሩዋት። ንጉሱ እና የመንግስት አስተዳደሩም ወደ ለንደን ዩናይትድ ኪንግደም ሸሹ። የተቃውሞ ዘመናቸውንም እዛው ሆነው ቀጠሉት።

©J.W. Cappelens arkiv©J.W. Cappelens arkiv

ከጥቂት የውጊያ ቀናት በኋላ ከኖርዌይ የቀረበ ብዙ ወታደራዊ ተቃውሞ አልነበረም። ፖሊስ በናዚ ቁጥጥር ስር ዋለ፤ ከናዚ ጋር የሚስማማ መንግስትም ተቋቋመ። ይህ መንግስት በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ አልነበረም።

ብዙ ኖርዌጂያዊያኖችም በውጊያው ጊዜ ህጋዊ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎች ያካሄዱ ነበር። አንዳንድ ቁጥጥች ያልተደረገባቸው መረጃዎች ለምሳሌ ጋዜጦች እና ትንንሽ በረሪ ጽህፈት ይበተኑ ነበር። በሌሎችም እርዳታ ምክንያት ህዝቡ ከናዚ ግዛት ወደ ስዊድን እና ዩናይትድ ኪንግደም እንዲሁም ሌሎች ሀገሮች ሊሸሽ ችሏል። ብዙ ሰዎችም ተይዘው ወደ እስረኛ ማከማቻ ቦታዎች ተወሰዱ።

ምንም እንኳን ሀገሪቷ ተወርራ የነበረ ቢሆንም አብዛኛው ሰው ወደ ተለመደው ስራው እንደዚሁም ልጆች ወደ ትምህርት ቤታቸው መሄድ ይችሉ ነበረ። ነገር ግን ምግብ፣ ልብስ እና ሌሎች እቃዎች በእርዳታ ራሽን መልክ ይሰጡ ነበር፤ ቀጣዩም ሁኔታ ያልረጋ ሆነ።

ከውጊያው በፊት ኖርዌይ ትልቅ የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴ ነበራት። በውጊያው ጊዜ ከ1940 እስከ 1945 አብዛኛዎቹ መርከቦች ከጀርመን ጋር ሲዋጉ ወደ ነበሩት ሀገሮች እቃ ሲያመላልሱ ነበረ። ለንደን ውስጥ የነበረው የኖርዌይ መንግስትም ጉዞውን ሲያቀናጅ ነበር። ከመርከቦቹ ግማሽ ያህሉ በቶርፒዶ(በውሃ ውስጥ ለመርከብ አውድማ የሚጓዝ ፈንጅ) ወይም ቦምብ ተመቱ። በውጊያው ጊዜ አራት ሺህ የሚያህሉ ኖርዌጂያዊያን ባህረኞች ተገድለዋል።

በውጊያው ምክንያት በአጠቃላይ አስር ሺህ የሚያህሉ ሴቶች እና ወንዶች ሞተዋል። ከእነዚህ 700 አካባቢ አይሁዶች ሲሆኑ ጀርመን እና ፖላንድ ወደ ነበሩት እሰር ቤቶች ተልከዋል።

ጀርመን በ8 ግንቦት 1945 ስለተሸነፈች ኖርዌይ ከእንደገና ነጻ ሀገር ሆነች። ከውጊያው በኋላ ሃምሳ ሺህ ኖርዌጂያዊያን በሀገር ክህደት ወንጀለኞች ሆነው ተገኝተዋል። እነዚህም ከናዚ ጋር ሲተባበር የነበረው የዴስነት ሀገራዊ ፓርቲ ማለትም ናሽናል ሳምሊንግ አባሎች የነበሩ ናቸው። ከውጊያው በኋላ ሃያ አምስት ሰዎች በአገር ክህደት ወንጀል ተከስሰው ሞት ተፈርዶባቸዋል።

©Sverre A. Børretzen/Scanpix©Sverre A. Børretzen/Scanpix

1945 በኋላ አገሪቷን መልሶ የማቋቋም ስራ ተጀመረ። ይህም በጣም እረፍት ያልነበረው ጊዜ ሆነ። የምርት ውጤት እና ወደ ወጪ የሚላኩ ዕቃዎች ጨምሩ። የንግድ መርከቦች ማጓጓዣም ዳግመኛም ተሰራ።

ብዙ ሰው ስራ አገኘ። ምንም እንኳን ደምወዝ ከፍተኛ ባይሆንም ድህነት ቀነሰ። አብዛኛው ሰው በጣም ደስተኛ እና ባለ ተስፋ ነበረ። አብዛኛዎቹ ሰዎች ኖርዌይን መልሶ በማቋቋም ስራ ላይ ለመሳተፍ የጓጉ ነበር። እኩልነት እና እኩል ክብር የሚሉት ቃላት ለህዝቡ አስፈላዚዎች ሆኑ። ምንም እንኳን እስከ 1950ዎቹ መጨረሻ አንዳንድ እቃዎች በእርዳታ መልክ ይሰጡ የነበረ ቢሆንም ኢኮኖሚው ግን ቀስ በቀስ ተሻሻለ።

ውጊያው ከተጠናቀቀ ከአስር አመታት በኋላ የአብዛኛው ሰው ኑሮ የሚያሻሽሉ ጥገናዎች (ታሀድሶ) ተደርጓል። የስራ ሰዓታት እንዲያጥር እና የእረፍት ጊዜ እንዲረዝም ተደረገ። በ1967 የሀገራዊ ደህንነት አዋጅ ስራ ላይ ዋለ። አዋጁ ለአረጋዊያን እና ታማሚዎችን የሚያጠቃልል ለሁሉም ዜጎች የሚሆን የገንዘብ ዋስትና ለማረጋገጥ ያለመ ነበር።

በኖርዌይ ውስጥ በተደረገ ወረራ እና ከውጊያ በኋላ በተደረገው ሀገርን መልሶ ማቋቋም እና ማህበራዊ ደህንነት የምትሰጥ ሀገር መፍጠር መካከል ያለው ትስስር ተወያዩ።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no