Intro
Amharisk • አማርኛ

ቀማሚዎች እና መድሃኒት ቤት የሚገኙ ምርቶች

ኖርዌይ ውስጥ የመድሃኒት መደብሮች በግል ቀማሚዎች የተያዙ ናቸው። ብዙ ቀማሚዎች የቀማሚዎች ማህበር አባላት ናቸው። የቀማሚዎች ሱቆች ፋርማሲስቶች እና በመድሃኒት አጠቃቀም የሰለጠኑ ሌሎች ሰዎችን ይቀጥራሉ። ከቀማሚዎች ሱቆች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎች ትክክለኛውን መድሃኒትና ሌሎች የሚያስፈልጉንን ነገሮች በማግኘት ሊረዱን ይችላሉ። በቀላል ህመሞች ህክምና እና የመከላልከያ መድሃኒቶች ላይ ጥሩ የሆነ ምክር ሊሰጡን ይችላሉ።

በቀማሚዎች ሱቅ መድሃኒቶች፤ ቫታሚኖዎች፣ የተለያዩ ክሬሞች፣ የእርግዝና መከላከያ፣ የእርግዝና ምርመራ፣ የመስንጠቅ እና የቁስል ጉዳት ለማከም የሚያስፈልጉ ነገሮች፣ የንጽህና እና ጽዳት እቃዎችን መግዛት ይችላሉ።

በቀማሚዎች ሱቅ የምታገኙት አንዳንድ የህክምና መሳሪያዎች ከሱቆች እና ነገዳጅ ማደያዎች ሊገዙ የሚችሉ ናቸው። ሊገዙ ከሚችሉት አንደኛ ምሳሌም ተራ የህመም ማስታገሻ ነው።

አንዳንድ የህክምና መሳሪያዎች ከቀማሚዎች ሱቅ በመግዛት እኔታችን ውስጥ ልንይዝ እንችላለን። ከታች የተዘረዘሩት ህክምና መድሃኒቶች እና መሳሪያዎች ከእነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው።

  • ፕላስተሮች
  • ለቁስል እና ጉዳት የሚሆኑ ከኢንፌክሽን የሚከላከሉ መድሃኒቶች
  • ተራ የህመም ማስታገሻ
  • መጠቅለያ እና ማሸግያ
  • የመከነ ኮምፕረስ
  • የአፍንጫ ጠብታ መድሃኒት

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no