Intro
Amharisk • አማርኛ

እርግዝናን መከላከል

የእርግዝና መከላከያ መንገዶች እርግዝና እንዳያጋጥም ልትጠቀምባቸው የምትችል የተለያዩ መንገዶችና አግባቦችን ያጠቃልላል። ለእናንተ በበለጠ የሚስማማችሁ የእርግዝና መንገዶችና አግባቦችን ያጠቃልላል። ለእናንተ በበለጠ የሚስማሟችሁ የእርግዝና መከላከያ ማግኘት አስፈላጊ ነው። ሐኪሞች፣ የጤና ረዳቶችና አዋላጅ ነርሶችን ስለ እርግዝና መከላከያ ምክር ሊሰጧችሁ ይችላሉ። በሐኪም ጽ/ቤት ህዝባዊ ክሊኒክ ወይም ሆስፒታል የሚሰራ ማንኛውም ሰው ሚስጢር የመያዝ ኋላፊነት አለበት።

 • ኮንዶም
 • ዲያፍራም / ማህጸን ውስጥ የሚገባ
 • የወንድ ዘርን ማምከኛ
 • ኦስትሮጄን የሌለው የእርግዝና መከላከያ ክኒን
 • ተራ የእርግዝና መከላከያ ክኒን
 • ቀለበት የእርግዝና መከላከያ
 • የእርግዝና መከላከያ ሽፋን
 • ትንሽ ኪኒን (ሚኒ-ፒል)
 • በማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ የሆርሞን እንክብል
 • በቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ
 • ማህጸን ውስጥ የሚቀበር የነሃስ እንክብል
 • መካን መሆን
 • ከድንገተኛ እርግዝና በኋላ የሚሰጥ የጽንስ መካላከያ
 • የማያስተማምን የጽንስ መከላከያ

ኮንዶም

ኮንዶም ማለት ለግንኙነት በተዘጋጀ ብልት ተዘርዝሮ የሚገባ በስስ ጎማ(ፕላስቲክ) የተሰራ ከረጢት ነው። ኮንዶም በሙላው የወሲብ ግንኙነት ጊዜ መደረግ አለበት። ኮንዶሙን ከአረፋ(ፎም) ወይም የወንድ ዘር ከሚያመክነው ክሬም ጋር መጠቀም የኮንዶሙን ዋስትና ይጨምረዋል። ኮንዶም በወሲባዊ ግንኙነቶች ከሚተላለፉት በሽታዎች እንደ ኤች.አይ.ቪ የመሳሰሉትን ይከላከላል። ኮንዶም በሁሉም ቦታዎች፤ ሱቆች፣ ፋርማሲዎች፣ የነዳጅ ማደያዎች ወዘተ ይሸጣል። ኮንዶም በአግባብ ከተጠቀምንበት በጣም አስተማማኝ ነው።

ድያፍራም / የማህጸን ሽፋን

ድያፍራም / የማህጸን ሽፋን ከሚለጠጥ ጎማ የተሰራ ሽፋን ሲሆን ሴትዋ ከብልትዋ ስር የምትቀብረው ነው። ይህም ከብልትዋ እስከ ማህጸንዋ ድረስ ያለውን ርቀት የሚሽፍን ነው። ድያፍራም/የማህጸን ሽፋን በተለያዩ መጠኖች የሚመጣ ስለሆነ ዶክተሩ ሊያስገባልሽ ይገባል። ዲያፍራም ወይም የማህጸን ሽፋን ከወንድዘር ማመከኛ ክሬም ጋር መጠቀም ይገባል። ድያፍራም/የማህጸን ሽፋንን የወሲባዊ ግንኙነት ከማድረጋችን በፊት በማንኛውም ጊዜ መደረግ ይችልላል። ከግንኙነቱ በኋላ ደግሞ ቢያንስ ለስድስት ሰዓታት ተደርጎ መቆየት ይኖርበታል። አብዛኛዎቹ ሴቶች ዲያፍራም/የማህጸን ሽፋንን ሊጠቀሙ ይችላሉ። ዲያፍራም/የማህጸን ሽፋን ከወንድ ዘር ማምከኛ ክሬም ጋር በሴትዋ ብልት ውስጥ አብሮ ከተደረገ ለጽንስ መከላልከያ ያስተማምናል።

ተራ የእርግዝና መከላከያ ክኒን

©Stephen Meddle/Rex Features/All Over Press©Stephen Meddle/Rex Features/All Over Press
ተራ የእርግዝና መከላከያ ክኒን ከ30 አመታት በላይ በገበያ ላይ ውሎ ይገኛል። ክኒኖቹ ሁለት የተለያዩ የሰው ሰራሽ የሆርሞን(እድገንጥር) አይነቶችን ይይዛሉ። እነዚህም ኦስትሮጅን እና ፕሮጅስትሮን ሲሆኑ በኦቫሪ ውስጥ የሚፈጠሩትን እድገንጥር ይመስላሉ። የተለያዩ የእርግዝና መከላከያ ክኒኖች የተለያዩ ይዘት ያላቸው አይነቶች የተዘጋጁ ናቸው። ለእናንተ የሚስማማችሁን አይነት ለማግኘት እና የእርግዝና መከለከያ ክኒን ማዘዣ ላይ ሐኪምዎ ይረዳዎታል። ተራ የእርግዝና መከላከያ እንቁላል እንዳይኖር ይከላከላል። እንቁላልም በማህጸን አካባቢ መጣበቅ አስቸጋኪ ያደርገዋል። ተራ የእርግዝና መከላከያ ክኒን በአግባቡ ከተጠቀምንበት በጣም አስተማማኝ ነው። ተራ የእርግዝና መከላከያ ክኒን ለመጠቀም የሐኪም ትዕዛዝ ያስፈልጋል።

የእርግዝና መከላከያ ቀለበት

የእርግዝና መከላከያ ቀለበት የሚለሰልስና የሚተጣጠፍ ቀለበት ሲሆን ሴትየዋ ራስዋ ወደ ብልትዋ ውስጥ የምታስገባው ነው። ይህ ቀለበት ምንም እንኳን ከእርግዝና መከላከያ ክኒን የሚያንስ ቢሆንም የኦስትሮጅን እና የፕሮጀስትሮን ይዘት አለው። ቀለበቱ ቀስ በቀስ እድገንጥርን (ሆርሞኖቹን) ይረጫል። የቀለበት የእርግዝና መከላከያ ለሦስት ሳምንታት በብልት ውስጥ ገብቶ ሊቆይ ይችላል። ከዚያ በኋላ ቀለበቱን በማውጣት ከአንድ ሳምንት በኋላ አዲስ ቀለበት ይገባል። ይህ ቀለበት እንቁላልን ይከላከላል። ቀለበቱን ለመጠቀም ቀላል ነው። የእርግዝና መከላከያ ቀለበት በሐኪም ትዕዛዝ ከፋርማሲ ሊገኝ ይችላል። በጣም አስተማማኝም ነው። የእርግዝና መከላከያ ክኒን ሊጠቀሙ የማይችሉት የቀለበት እርግዝና መከላከያ መጠቀም አይችሉም።

የሽፋን እርግዝና መከላከያ

የሽፋን እርግዝና መከላከያ በእርግዝና መከላከያ ክኒን የሚገኝ አንድ አይነት ኦስትሮጅንና ፕሮጅስትሮን በአነስተኛ መጠን ይገኛል። እነዚህ አድገንጥር በቆዳ አማካኝነት ይሰራጫሉ። እነዚህ ሽፋኖች ለሦስት ሳምንታት ያህል በተመሳሳይ የሳምንቱ ቀናት ይቀየራሉ። በሦስት ሳምንታት ሦስት ሽፋኖች ከተጠቀማችሁ በኋላ አዲስ ሽፋን በተመሳሳይ ቀን ከማድረጋችሁ በፊት ለአንድ ሳምንት ያህል እረፍት ውሰዱ። ሽፋኖቹ እንቁላልን ይከለክላሉ። እነዚህ ሽፋኖች በሐኪም ትዕዛዝ ፋርማሲ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ። ልክ እንደ እርግዝና መከላከያ ክኒን አነስተኞች ናቸው።

አነስተኛ ክኒን (ሚኒፒል)

አነስተኛ ክኒን (ሚኒፒል) አንድ አይነት አድገንጥር(ሆርሞኖች) ማለትም ፕሮጅስትሮን ይይዛሉ። ይህ ንዑስ ክኒን በየቀኑ በየአንድ ሰዓቱ መወሰድ ይኖርበታል። ይህንን ክኒን ሳይወስዱ ከለሱት እና በሚወስዷቸው ሁለት ክኒኖች መካከል ከ27 ሰዓታት በላይ ከሆነ እርግዝናን የሚከላከል ተጨማሪ የመከላከያ አይነት ለ14 ሰዓታት መጠቀም አለባቸው። ክኒኑን መውሰድ ግን እንደተለመደው መቀጠል ይኖርበታል። አነስተኛ ክኒንን (ሚኒፒልን) ለማግነት የሐኪም ትዕዛዝ ያስፈልጋል።

ማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ ሆርሞናዊ(የአድገንጥር) እንክብል

ማህጸን ውስጥ የሚቀመጠው እድገንጥር(የሆርሞን) እንክብል የማህጸን የውስጥ ስርዓት - አዩኤስ (intrauterine system (IUS)) ወይም የማህጸን ውስጥ መሳሪያ - አዩዲ (intrauterine device(IUD)) ተብሎ ይጠራል። በሐኪሙ የሚገባ ትንሽ ነገር ነው። የዚህ ሽቦ መብባት በመጠኑ ምቾት ባይኖረውም በፍጥነት ይተወዋል። አለመመቸቱ ከቀጠለ ግን ሐኪምዎን ያናግሩ። ይህ ሆርሞናዊ(እድገንጥራዊ) ሽቦ ማህጸን ውስጥ የሚኖረው የእንቁላል እድገት ያስተጓጉለዋል። የወንዱ ዘርም ወደ እንቁላሉ እንዳይገባ ያደርገዋል። የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን እንዳይጓዝ ይከላከላዋል። ይህ ሆርሞናዊ(እድገንጥርዊ) እንክብልን ለብዙ አመታት ለመጠቀም ውጤታማ ነው። ይህም እርግዝና የምንከላከልበት አስተማማኝ መንገድ ነው።

የቆዳ ስር የሚቀበረው የእርግዝና መከላከያ

በኖርዌይ ገበያ በቆዳ ስር የሚቀበሩ ሁለት የእርግዝና መከላከያ አይነቶች አሉ። የክብሪት እንጨት የሚያህሉ ሲሆኑ የፕሮጅስቶጅን ሆርሞን ውህድ አለው። በአይነቱ ላይ በመመርኮሽ ለሦስት ወይም አምስት አመታት በልጅቷ የጡንቻ ቆዳ ላይ ይቀበራል። ይህ በሐኪሙ ቢሮ ይወክላል። ይህ የሚቀበረው ዘንግ ለማድረግ የሚፈልገውን እንቁላል በመከልከል የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን እና የማህጸን መስመር እንዳይደርስ የማህጸን መግቢያ ላይ ተጽዕኖ ያደርጋል። በቆዳ ስር የሚቀበር የእርግዝና መከላከያ ዘንግ በጣም አስተማማኝ የእርግዝና መከላከያ ዘንግ በጣም አስተማማኝ የእርግዝና መከላከያ ነው።

ማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ የነሃስ እንክብል

©Steinar Myhr/Samfoto©Steinar Myhr/Samfoto
ማህጸን ውስጥ የሚቀመጥ የነሃስ እንክብል ማህጸን ስርዓት ወይም የማህጸን ውስጥ መሳሪያ ተብሎ ይጠራል። ልክ እንደ ሆርሞናዊ(እድገንጥራዊ) እንክብል ሽቦ ወደ ማህጸን ውስጥ የሚገባ ነው። ይህ የጽንስ መከላከያ መንገድ እንቁላል ወደ ማህጸን እንዳይጣበቅ ይከለክላል። የወንዱ ዘር ወደ ማህጸን እንዳይጓዝም ይከላከላል። ይህ እንክብል ከአምስት እስከ አስር አመታት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ውጤታማ ሲሆን ጥሩ የእርግዝና መከላከያም ነው። ኮፕራዊ እንክብል ከበድ ያለ የወር አበባ ሊያመጣና አልፎ አልፎም የወር አበባ ህመም ሊያስከትል ይችላል።

ማምከን

የመውለድ መከላከያ መጨረሻ ዘዴ ነው። መካን የሆነ ወንድ ወይም ሴት መውለድ አይችልም/አትችልም። አንዴ መካን ከሆነ መልሶ ፍሬ ለማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ስለዚህ መካን ከመደረግ በፊት በጥንቃቄ ሊታሰብበት ይገባል።

ከድንገተኛ እርግዝና በኋላ የሚሰጥ መከላከያ

ሴትዋ የወር አበባ ሳይኖራት ወሲብ ብትፈጽም የማርገዝ እድሏ ወደ 20% አካባቢ ነው። በዚህ ወቅት ያለ እርግዝና መከላከያ ወሲባዊ ግንኙነት ብትፈጽም ያለ ሐኪም ትዕዛዝ ከድንገተኛው እርግዝና በኋላ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ ከፋርማሲ መግዛት ትችላለች። እነዚህ ክኒኖች ወሲብ በተፈጸበት በ72 ሰዓታት መወሰድ ያለባቸው የተለያዩ ሆርሞኖችን በብዛት ይይዛል። እርጉዝ መሆንዋን ለማረጋገጥ ከሦስት ወይም አራት ሳመንታት በኋላ አንዴ ለምርመራ ወደ ሐኪም መሄድ አስፈላጊ ነው። እርግዝናው ከቀጠለ እነዚህ ሁኔታዎች የተረገዘውን ልጅ ሊጎዱት ይችላሉ። እንዲሁም አስተማማኝ ያልሆነ ፆታዊ ግንኙነት ከተፈጸመ በአምስት ቀናት ውስጥ እንክብል (ኮይል) በማስገባት እርግዝናን መከላከል ይቻላል።

የማያስተማምን የእርግዝና መከላከያ አገባብ

ከወር አበባ በኋላ ያለው አስተማማኝ ጊዜ

በንድፈ ሀሳብ መሰረት የሴት ልጀ እንቁላል ለእርግዝና ዝግጁ በሚሆንበት ወቅት ጾታዊ ግንኙነት ባለማድረግ እርግዝናን መከላከል ይቻላል። ነገር ግን የዑደቱ ርዝመት እና እንቁላሉ ዝግጁ በሚሆንበት ጊዜ ከሴቶች ወደ ሴቶች ስለሚለያይ ይህ መንገድ እጅጉን በጣም የማያስተማምን መንገድ ነው።

ጾታዊ ግንኙነትን የማቋረጥ ዘዴ

የወንዱ ዘር ከመፍሰሱ በፊት ጾታዊ ግንኙነትን ማቆም ጽንስን ሊከላከል ይችላል። ነገር ግን ይህ ዘዴ ዋስትና የለውም። ምክንያቱም አንዳንድ የወንዱ ዘሮች ፈሳሹ ከመፍሰሱ በፊት ወደ ሴቷ ብልት ሊገቡ ይችላሉ። የወንዱ ዘር በሴቷ ብልት አካባቢ ባለው ቆዳ ከፈሰሰም ወደ ብልቷ ውስጥ ሊገባ ይችላል።

Ansvarlig for disse sidene J.W. Cappelens Forlag AS. Læremidlet er utviklet med støtte fra Utdanningsdirektoratet. Tilbakemeldinger: intro@cappelendamm.no